የትራፊክ አደጋ ላይ የሚያተኩር ጥናት ሊካሔድ ነው

0
948

የትራፊክ አደጋ በእየለቱ በርካቶችን በሚነጥቅባት ኢትዮጵያ የአደጋው መንስኤና መፍትሔ ላይ ትኩረት የሚያደርግ ጥናት ሊካሔድ መሆኑ ታውቋል።
ጥናቱ የአዲስ አዳማ የክፍያ መንገድን ጨምሮ በአገሪቷ ባሉ በተመረጡ 2000 ኪሎ ሜትር መንገዶች ላይ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

የትራንስፖርት ሚንስትሯ ዳግማዊት ሞገስ የካቲት 27/2011 ጥናቱን ከሚያካሂደው ኢፒቲአይኤስኤ ከተሰኘ ዓለም ዐቀፍ የስፔን ድርጅት ጋር ስምምነት ተፈራርመዋል ።

ለጥናቱ የሚያስፈልገው ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ነው የተባለም ሲሆን፣ ገንዘቡ ከዓለም ባንክ በሚገኝ ድጋፍ የሚሸፈን ይሆናል።

በመንገድ ንድፍ፣ ግንባታ፣ ጥገና እና የመንገድ ሀብት ማስተዳደር ሒደት ለአደጋ መከሰት ምክንያት የሚሆኑ ጉድለቶች ስለመኖራቸው ይፈትሻል የተባለው ጥናቱ፣ በአሽከከርካሪ መንጃ ፍቃድ አሰጣጥ እና የተሸከርካሪ ደረጃዎችና ዓይነቶች ላይ የሚያተኩሩ ክፍተቶች ላይም አፅንኦት እንደሚሰጥ ተገልጿል።

የጥናቱ ውጤት የትራፊክ አደጋን ሳይንሳዊ በሆነ ጥናት በመታገዝ የመፍትሔ እርምጃ ለመውሰድ አጋዥ ይሆናል የሚል ተስፋም ተጥሎበታል።

ቅጽ 1 ቁጥር 17 የካቲት 30 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here