ዝርፊያ ሲፈፅሙ የነበሩ 8 ቡድኖች ተያዙ

0
524

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በቡድን ተደራጅተውና በጦር መሳሪያ ታግዘው ዝርፊያ ሲፈፅሙ ነበሩ ያላቸውን ስምንት ቡድኖችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አሳወቀ።

ተጠርጣሪዎቹ በቡድን ተደራጅተው የተለያዩ ወንጀሎችን ሲፈፅሙ ነበሩ የተባለ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ የተለያዩ ክፍለ ከተሞች ላይ በቤት፣ በተሽከርካሪ እና በተለያዩ የዘረፋ ወንጀሎች ተሰማርው ቆይተዋል ሲል ኮሚሽኑ ገልጿል።

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ሲውሉ 8 ሽጉጦች፣ 4 የተሰረቁ ተሽከርካሪዎች፣ ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች፣ ጥራዝ ቼኮች እና የኢትዮጵያ ብርን ጨምሮ የውጭ አገራት ገንዘቦች አብረው መያዛቸውም ታውቋል።

የወንጀሎቹ አቀነባባሪ የተባለውም ከአገር ሊወጣ ሲል ተይዟል ተብሏል።

ከከተማዋ መስፋፋት ጋር በተያያዘ በቅርብ የተመሠረቱ ሠፈሮችና በብዛት ነዋሪዎች የከተሙባቸውን የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ደኅንነት ለማስጠበቅ ፖሊስ በትኩረት እሰራለሁ ያለ ሲሆን፣ የማኅበረሰብ ዐቀፍ ፖሊስ አገልግሎትን በማጠናከር ቀድሞ መከላከሉ ላይ እበረታለሁም ብሏል።

ቅጽ 1 ቁጥር 17 የካቲት 30 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here