የአማራ ዓለም ዓቀፍ ልማት ትብብር ተመሠረተ

0
444

የአማራን ሕዝብ በምጣኔ ሀብት ረገድ ለማገዝ ያለመ ‹‹የአማራ ዓለም ዓቀፍ ልማት ትብብር›› በሰሜን አሜሪካ መመስረቱ ተሰማ።

የትብብሩ ዓላማ በአማራ ሕዝብ ላይ በተለይም በምጣኔ ሀብት ረገድ የተጋረጡትን ችግሮች ለመቅረፍ እንደሆነ ተነግሮለታል። ስለሆነም ትብብሩ ትኩረቱን በምጣኔ ሀብቱ ዘርፍ ላይ እንደሚያደርግ ከወዲሁ አሳውቋል።

የአጭርና ረጅም ጊዜ እቅዶችን ነድፌያለሁ ያለው የልማት ትብብሩ የመጠጥ ውሃ፣ የጤና፣ የመማሪያ ክፍሎች እና መጠለያ ችግሮችን ለማቃለል እንዳሰበም ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።

ለዚህም በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የአማራ ተወላጆችንና ወዳጆችን በማስተባበር የአማራን ሕዝብ ችግሮች ለመቅረፍ እንደሚንቀሳቀስ አክሏል።
አሁን ላይ ተፈናቅለው ለሚገኙ የክልሉ ተወላጆች አስቸኳይ የምግብና መጠለያ ድጋ የማድረጉን ሥራ በአጭር ጊዜ ዕቅድ መያዙንም አሳውቋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 17 የካቲት 30 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here