የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ተፈናቃዮች ቁጥር እያሻቀበ ነው

0
608

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ተፈናቃዮች ቁጥር እየጨመረ መሆኑንና፣ ከእነዚህም ውስጥ ሕጻናት፣ ነፍሰ ጡር ሴቶችና አዛውንቶች እንደሚገኙበት ታውቋል፡፡

ህጻናትና ሴቶች ለብርድና ለምግብ እጥረት እየተዳረጉ መሆኑንና መጸዳጃ ቤትም አለመኖሩን የሚናገሩት ተፈናቃዮቹ፤ የጤና ባለሙያ አንድ ቀን መጥቶ ጎብኝቷቸው እንደማያውቅም አሳውቀዋል፡፡ በዚህም ምክንያት በግጭቱ ሕይወታቸው ያለፈው አልበቃ ብሎ አሁንም በመጠለያ ጣቢያው ጤንነቱ ባልተጠበቀ ሁኔታ በመኖራቸው ሳቢያ በሽታ በመከሰቱ የሰዎች ሕይወት ማለፉን ለቢቢሲ አማርኛ ተናግረዋል።

በአንድ ቤት በርካታ ሰዎች በመኖራቸው ለከፋ ወረርሽኝ ከመዳረግም ባሻገር ህጻናትና ሴቶችም ለጥቃት ሊጋለጡ እንደሚችሉ የሚናገሩት ተፈናቃዮቹ መንግሥት በፍጥነት እርምጃ ሊወስድ እንደሚገባ ጠይቀዋል፡፡

“የሚሰጠው ምግብ በቂ አይደለም፤ አርሶ ለሰው ሲተርፍ የነበረው አርሶ አደር በዚህ ሁኔታ በእርዳታ በመኖሩ ለስነ ልቦና ችግር ተዳርጓል” ሲሉም ያክላሉ፡፡

ቅጽ 1 ቁጥር 18 የመጋቢት 7 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here