እስረኞችን ለማስለቀቅ መንግሥት ከታንዛኒያ ጋር እየተደራደረ ነው

0
306

በታንዛኒያ እስር ቤት የሚገኙ ከ450 በላይ ኢትዮጵያዊያንን ለማስፈታት የኢትዮጵያ መንግሥት ከታንዛኒያ መንግሥት ጋር ድርድር እያደረገ ነው፡፡

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ነብያት ጌታቸው ትናንት አርብ ረፋድ ለመገናኛ ብዙኃን አውታሮች በሰጡት መግለጫ በሕገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ በታንዛኒያ መንግሥት ተይዘው እስር ላይ የነበሩ 50 ኢትዮጵያዊያን መጋቢት 5/2011 ታንጋ ከሚባለው የአገሪቱ እስር ቤት እንዲለቀቁ ሆኗል፡፡ ይሁንና አሁንም ከ450 በላይ ኢትዮጵያዊያን በተለያዩ የታንዛኒያ እስር ቤቶች እንደሚገኙ የገለጹት ነብያት ዜጎችን አስፈትቶ ወደ አገር ውስጥ ለመመለስ ከታንዛኒያ መንግሥት ጋር ድርድር እየተደረገ ስለመሆኑም አሳውቀዋል፡፡

በተያያዘ ዜና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጅዳ በሚገኘው ቆንጽላ ጽሕፈት ቤቱ በኩል በሳኡዲ አረቢያ መንግሥትና ከዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ጋር በመተባበር በሳኡዲ አረቢያ ያለመኖሪያ ፈቃድ ይኖሩ የነበሩ 447 ኢትዮጵያዊያንን በፈቃዳቸው በሳምንቱ አጋማሽ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ሆኗል ተብሏል። በዚህም በሳኡዲ የነበሩና ለመመለስ የፈቀዱ አንድ ሺሕ 800 ኢትዮጵያዊያንን በአራት ዙር ወደ አገራቸው ለመመለስ እየተሰራ መሆኑንም ቃል አቀባዩ አክለዋል፡፡

ቅጽ 1 ቁጥር 18 የመጋቢት 7 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here