ትጥቃቸውን ፈተው በጦላይ ወታደራዊ ካምፕ የሚገኙ አንድ ሺሕ የሚሆኑ የቀድሞ የኦነግ ሰራዊት አባላት የረሃብ አድማ አደረጉ።
ወታደሮቹ ለረሃብ አድማው እንደምክንያት የሚጠቅሱት፣ በወታደራዊ ካምፑ ውስጥ የአያያዝ ሁኔታው በጣም አስከፊ በመሆኑና በምግብ እጥረት እንዲሁም በንፅህና ችግር እየታመምን ነው የሚል መሆኑ ተሰምቷል።
ከዚህም በተጨማሪ ወታደሮቹ ወደ ሕብረተሰቡ ከመቀላቀላቸው በፊት ይሰጣቸዋል የተባለው ሥልጠና እና ሌሎች ቃል የተገቡላቸው ነገሮች አለመፈፀማቸው ቅሬታቸውን እንዳባባሰው ተናግረዋል።
ወታደሮቹ ትጥቅ ፈተው ወደ ካምፕ እንዲገቡ ሲያሸማግል የነበረው ኮሚቴ አባል ፖለቲከኛው በቀለ ገርባ ሥልጠና ላይ የሚገኙትን የቀድሞ የኦነግ ሠራዊት አባላት ያሉበትን ሁኔታ ለማየት ከክልሉ መንግሥት ፈቃድ እየጠበቁ እንደሆነ ታውቋል። ኦነግና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የደረሱትን ስምምነት ተከትሎ ነው የኦነግ ሠራዊት አባላት ወደ ሥልጠና ካምፕ ሲገቡ የነበረው።
ቅጽ 1 ቁጥር 18 የመጋቢት 7 ቀን 2011