በጋምቤላ አንድም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ፈቃድ የለውም

0
480

በጋምቤላ ሕጋዊ እውቅና የተሰጠው አንድም የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ባይኖርም በርካታ ተቋማት በሕገ ወጥ መንገድ እያስተማሩ ነው ሲል የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ አሳወቀ፡፡

ኤጀንሲው መጋቢት 5/2011 ለጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳር ጽሕፈት ቤት በጻፈው ደብዳቤ ክልሉ ሁሉም የግል ተቋማት ፈቃድና እውቅና የሌላቸው መሆናቸውን አውቆ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል፡፡ በክልሉ አንድም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ፍቃድ ለማግኘት ለኤጀንሲው አለማመልከቱን ያሳወቀው ኤጀንሲው ይሁንና በክልሉ በርካታ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያለ ፍቃድና እውቅና እያስተማሩ መሆኑን አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡ ለማሳያ በሚልም ኹለት ተቋማትን ጠቅሷል፡፡

ኤጀንሲው አክሎም ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እውቅናና ፈቃድ የመስጠቱ ሥልጣን የኤጀንሲው ብቻ መሆኑን አመልክቷል፡፡ በመሆኑም በክልሉ ያለ ፈቃድ እያስተማሩ ያሉ አካላት በሰዎች ገንዘብ፣ ጊዜና ስነ ልቡና እየቀለዱ በመሆኑ የክልሉ መንግሥት በሕገ ወጦቹ ላይ እርምጃ በመውሰድ ለዜጎቹ ጥብቅና እንዲቆም ጠይቋል፡፡

ከእነዚህ የትምህርት ተቋማት የሚገኘው ማንኛውም የትምህርት ማስረጃ ሕገ ወጥና ቅቡልነት የማኖረው መሆኑንም ኤጀንሲው ከወዲሁ አስጠንቀቅቋል፡፡

ቅጽ 1 ቁጥር 18 የመጋቢት 7 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here