2 ደቂቃ አርፍዶ ከሞት መትረፍ!

0
419

ባሳለፍነው እሁድ መጋቢት 1/2011 ጠዋት 157 ሰዎችን የያዘውና ንብረትነቱ የኢትዮጵያ መንግሥት የበረው የበራራ ቁጥር ኢቲ 302 ቦይንግ ማክስ 8 አውሮፕላን ከአዲስ አበባ ወደ ኬንያ ናይሮቢ የጀመረው በረራ በእንጭጩ መቀጨቱ ይታወሳል።

ምክንያቱ ደግሞ ጠዋት 2፡38 የተነሳው አውሮፕላኑ ከስድስት ደቂቃ በኋላ እስካሁን ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ባጋጠመው የመከስከስ አደጋ ነው። በአደጋው የ157ቱም ሰዎች ሕይወት ማለፉ ለኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆን የመላው ዓለም ሀዘን ሆኖም ሰንብቷል። በበረራው የ35 አገራት ዜጎች የነበሩ መሆኑም ሀዘኑን የብዙዎች አድርጎታል።

ይሁንና በዕለቱ ኹለት ደቂቃ አርፍዶ ቦሌ ዓለም ዐቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የደረሰው ክሪካዊው አንቶኒስ ማቭሮፖሎስ ከአደጋው ሀዘን ባሻገር የበርካቶችን ቀልብ ስቦም ሰንብቷል። አንቶኒስ ኹለት ደቂቃ ማርፈዱነ ተከትሎ ወደ ናሮቢ ያደርገው የነበረው በረራ በማምለጡም ተበሳጭቶ በአየር መንገዱ ግቢ ብስጭቱን ሲገለልጽ እንደነበር ተሰምቷል። ነገር ግን ‹ትረፍ› ያለው ሆነና ያመለጠው አውሮፕላን ከ100 ኪሎ ሜትር በረራ በኋላ ቢሾፍቱ አካባቢ ሲከሰከስ ለአንቶኒስ ‹ለካ ማርፈድም በጎ ነገር አለው እንዴ› አስብሏል።

ብዙዎችም የተከሰከሰው አውሮፕላን ያመለጠውን ግሪካዊ ‹እድለኛ በመሆኑና ቀኑ ባለመድረሱ ተረፈ› ሲሉ በማኅበራዊ የመገናኛ አውታሮች ፎቶ ግራፉን ሲቀባበሉት ሰንብተዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 18 የመጋቢት 7 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here