የአፄ ቴዎድሮስ ሹሩባ ተመለሰ

0
1086

በ1860 በኢትዮጵያ እና በእንግሊዝ መካከል በተደረገው ጦርነት ሕይወታቸውን የሰውት የአፄ ቴዎድሮስ ሽሩባ ኢትዮጵያ ከእንግሊዝ የጦር ሙዚየም ተተረከበች። በኢትዮጵያ እና በእንግሊዝ መንግሥት የተደረገው ድርድር ፍሬ አፍርቶ ኹለት ዘለላ የንጉሠ ነገሥቱ ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ሹሩባ ከአንድ ክፍለ ዘመን ተኩል በላይ ከኖረበት እንግሊዝ አገር ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ ተወስኗል።

በእንግሊዝ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ፍሰሐ ሻውል ከእንግሊዝ ብሔራዊ የጦር ሙዚየም ኃላፊ ብርጋዴር ጀስቲን ማሲጄስወስኪ ጋር ውይይት ካደረጉ በኋላ ጉንጉን ፀጉሮቹ እንዲተላለፉ ሆኗል። ኹቱ ጉንጉኖች የተለያየ ርዝመት ላቸው ሲሆን፣ በጊዜ ብዛት መጠንና ርዝመታቸው የመቀነስ ሒደት ስለማሳየቱም ተነግሯል። በርክክቡ ወቅት የባሕልና ቱሪዝም ሚንስትር ሒሩት ካሳው (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 20 መጋቢት 14 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here