የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና ዋሊያ ቢራ አክሲዮን ማኅበር የ56 ሚሊዮን ብር የብቸኛ ስፖንሰር ሺፕ ስምምነት ተፈራርመዋል።
መጋቢት 11 የተካሔደው የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት ፊርማ ለአራት ዓመታት የሚዘልቅ ነው። በእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ እና በዋሊያ ቢራ መካከል የተደረሰው የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት ለኢትዮጵያ የወንድ እና የሴት ብሔራዊ ቡድኖች የሚሆን ነው።
ሰሞነኛው ስምምነት ከዚህ በፊት ከነበረው ውል በተለየ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከቢራ እና ማልት መጠጦች ውጪ ከሌሎች የመጠጥ ተቋማት ጋር የስፖነሰር ሺፕ ስምምነት መፈራረምን የሚፈቅድ ስለመሆኑም ከእግር ኳስ ፌደሬሽኑ የተገኘው መረጃ አመልክቷል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት ኢሳያስ ጅራ በፌዴሬሽኑ እና በዋሊያ ቢራ መካከል የተፈረመው የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት በምግብና መጠጥ ላይ የወጣውን አዋጅ መሰረት አድርጎ የተፈፀመ ስለመሆኑም አውስተዋል።
ዋሊያ ቢራ አክሲዮን ማኅበር ከዚህ ቀደምም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ላለፉት አራት ዓመታት በ56 የሚሊዮን ብር ስፖንሰር ማድረጉን መረጃዎች አመልክተዋል።
ቅጽ 1 ቁጥር 20 መጋቢት 14 ቀን 2011