መኢአድ ለ8 ዓመታት ከፓርቲው ከተገለሉ አመራሮች ጋር እርቅ ፈጠርኩ አለ

0
592

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ላለፉት 8 ዓመታት ራሳቸውን ከፓርቲው አግልለው ከቆዩ አመራሮች ጋር እርቅ በመፍጠር በጋራ ለመስራት መስማማቱን አስታወቀ።

የመኢአድ አመራሮች በመካከላቸው ያለውን አለመግባባት በመፍታት በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን የገለጹ ሲሆን፣ በነበረው አለመግባባት ላለፉት 8 ዓመታት ራሳቸውን ከድርጅቱ አግልለው ከቆዩ አመራሮች ጋር በተደረገ ውይይት መስማማት ላይ መደረሱን አሳውቋል።

ሊቀ መንበሩ በዛብህ ደምሴ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ በስምምነቱ ከዚህ በፊት በፓርቲው ውስጥ በነበረው የአቋም ልዩነት ከድርጅቱ ራሳቸውን አርቀው የቆዩ አመራሮችና አባላት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲመለሱ ተወስኗል።

የቀድሞ የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አባል እና በተደረገው ዕርቀ ሰላም ፓርቲውን የተቀላቀሉት ማሙሸት አማረ በበኩላቸው ለኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በተናጥል ሳይሆን በጋራ የሚሰራ የተባበረ ክንድ ያስፈልጋል ብለዋል።

ድርጅቱ በ1991 ከመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት (መአህድ) ወደ መኢአድ መቀየሩ ይታወሳል።

ቅጽ 1 ቁጥር 20 መጋቢት 14 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here