ኢትዮ ቴሌኮም ለተፈናቃዮች የ40 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

0
435

ኢትዮ ቴሌኮም በተለያዩ ምክንያቶች ከመኖሪያ ቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል የ40 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን አሳወቀ። ኩባያንው ድጋፍ ለሚሹ ኢትዮጵያዊያን ገንዘብ ማሰባሰቢያ የሚሆን የአጭር ጽሑፍ መልዕክት አገልግሎትም ይፋ አድርጓል። ሰዎች በ 6020 የአጭር የጽሑፍ መልዕክት ላይ A ን በመላክ የኹለት ብር ድጋፍ ማድረግ ይችሉ ዘንድም መስመሩን ይፋ አድርጓል።

የአጭር ጽሑፍ መልዕክት መቀበያውን ማዘጋጀት ያስፈለገው በአገሪቱ የተለያዩ ማዕዘናት ያሉ ኢትዮጵያዊያን ለተፈናቃዮች ድጋፍ ለማድረግ እየተረባረቡ በመሆኑ ድጋግፉን ለማቀናጀት ነው ተብሏል። በተጨማሪም የተለያዩ አካላት ይህንኑ በአጭር መልዕክት ገንዘብ የመሰብሰቢያ አማራጭ እንዲዘጋጅ ሲጠይቁ መክረማቸውን መነሻ በማድረግ ነው።

በአጭር የጽሑፍ መልዕክት በኩል የሚሰበሰበው የገንዘብ ድጋፍ ለብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ገቢ እንደሚሆን ያሳወቀው ኢትዮ ቴሌኮም በዚህ መስመር የሚሰበስበውን ገንዘብ በተመለከተ በየጊዜው ወቅታዊ መረጃን ለሕዝቡ እያሳወቀ እንደሚሔድም አመልክቷል።

ኩባያንው ባሳለፈው ውሳኔ ለተፈናቃዮች ያደረገውን የ40 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለኮሚሽኑ ስለማስረከቡም ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 20 መጋቢት 14 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here