ተራዝሟል!

0
789

አራተኛው የሕዝብና ቤት ቆጠራ በተያዘለት ጊዜ ይካሔድ አይካሔድ የሚለው በርካቶችን ጎራ ለይተው እንዲከራከሩ ሲያደርጉ ከነበሩ አገራዊ ጉዳዮች መካከል ዋነኛው ነው።

ቆጠራው ቀደም ብሎ በወጣለት መርሀ ግብር መሰረት ከመጋቢት 29 እስከ ሚያዚያ 30 ይካሔዳል መባሉ ይታወሳል። ይሁንና አሁን ላይ በኢትዮጵያ ካለው የጸጥታ ችግርም ሆነ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች መፈናቀል ጋር ተያይዞ ቆጠራው መካሔድ የለበትም የሚል ተቃውሞ ሲስተናገድበትም ከርሟል።

መንግሥት በበኩሉ ለቆጠራው በቂ ዝግጅት አድርጌያለሁ፣ የሚያሰጋ የፀጥታ ችግርም የለም እንዲሁም ተፈናቃዮችም ባሉበት ይቆጠራሉ የሚል ምላሽ በመስጠት ከርሟል። ይሁን እንጂ ቆጠራው መራዘም አለበት የሚለው ተቃውሞም ጠንክሮ ሰንብቷል።

ይህን ተከትሎ በምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን የሚመራው የሕዝብና ቤት ቆጠራ ኮሚሽን መጋቢት 9/2011 ባካሔደው አስቸኳይ ስብሰባ አራተኛውን የሕዝብና ቤት ቆጠራ ለማካሔድ የተደረገውን ዝግጅት ከገመገመ በኋላ ቆጠራው ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ውሳኔ አሳልፏል።

ምክንያቱም የቆጠራውን ዓላማና ግብ በአስተማማኝ ሁኔታ ለማሳካት የሚያስችሉ ተግባራት የተሟሉ ባለመሆናቸው፣ ማለትም በየአካባቢው ለሥራው መሳካት በተገቢው ሁኔታ መጠናቀቅ የሚገባቸው ተግባራት ባለመጠናቀቃቸው እና ተጨማሪ ጊዜ በማስፈለጉ መሆኑም ተገልጿል።

የኮሚሽኑ የይራዘም ውሳኔ ሐሳብም ለተወካዮችና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች እንዲቀርብ በአብላጫ ድምፅ መወሰኑ በሳምንቱ በማኅራዊ የትስስር ገጾች ሰፊ ሽፋን ካገኙ ሰሞነኛ ጉዳዮች መካከል ናቸው።

ቅጽ 1 ቁጥር 20 መጋቢት 14 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here