10ቱ የሰብአዊ ቀውስ ሥጋት የተደቀነባቸው አገራት

0
683

ዓለም አቀፉ ሬስኪዩ ኮሚቴ የድንገተኛ ምላሽ ኤክስፐርቶች በዲሴምበር 2018 (እ.አ.አ) ባወጡት የአገራት የሰብኣዊ ቀውስ ሥጋት ትንበያ ሪፖርት የአገር ውስጥ መፈናቀልና ስደት እንደሚያስከትል ተንብየዋል። በዓለም ላይ ከዚህ በፊት ባልታየ ሁኔታ የአገር ውስጥ መፈናቀል እንደሚያጋጥም የተተነበየ ሲሆን በእነዚህ አስቸጋሪ አገራት የሰዎች ግጭት እና ሰው ሰራሽ ችግር ሕይወትን አዳጋች እንደሚያደርጉት ሪፖርቱ ጠቁሟል።

በዚህ ሪፖርት መሰረት 10 የዓለማችን አገራት በጣም የከፋ የሰብኣዊ ቀውሰ ያጋጠማቸውና የሚያጋጥማቸው ከተባሉት መካከል ኢትዮጵያ በዘጠነኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን በ2018 (እ.አ.አ) 1 ነጥብ 4 ሚሊዮን የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች የተመዘገቡ ሲሆን ይህም በዓለማችን ካሉት አገራት የሚስተካከለው አልተገኘም።

በተጨማሪም ሪፖርቱ ኢትዮጵያ በ2019 የበለጠ ብሔርን (ጎሳን) መሰረት ያደረገው ግጭት እንደሚቀጥል፤ ይህም ለበለጠ የሕዝብ በአገር ውስጥ መፈናቀልና ምግብ ዋስትና ማጣት እንደሚያጋልጥ ተተንብዮአል።

24 ሚሊዮን ሰብኣዊ እርዳታ ፈላጊ የሆኑ ተፈናቃዮች ያሏት የመን ሰብዓዊ ቀውስ ስጋት ከተደነቀነባቸው አገራት ቀዳሚ ስትሆን ከኢትዮጵያ በመቀጠል 1 ነጥብ 4 ሚሊየን የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ያሏት አፍጋኒስታን ሶስተኛ ደረጀን ይይዛለች።

ቅጽ 1 ቁጥር 20 መጋቢት 14 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here