ኢትዮጵያ በምጣኔ ሀብት ዘርፍ አጠቃላይ የአገሪቱን አቅጣጫ የሚጠቁም ጥናት እያካሔደች መሆኑን አሳወቀች።
ይህ የተባለው የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የዲፕሎማሲ ማኅበረሰብ አባላት ማብራሪያ በተሰጠበት ወቅት ነው።
ማብራሪያውን የሰጡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሂሩት ዘመነ አጠቃላይ የአገሪቱን የምጣኔ ሀብት አቅጣጫ የሚጠቁም ጥናት እየተካሔደ ነው ያሉ ሲሆን፣ ሲጠናቀቅ ለሕዝብ ይፋ እንደሚሆን ገልፀዋል።
መንግሥት ያለበትን የእዳ ጫና በማቃለል እና የበጀት ቋትን በማጠናከር ረገድ ስኬታማ ተግባራትን ማከናወኑንም ተናግረዋል።
‹‹ወደ ላቀ የምጣኔ ሀብት እምርታ የሚያሸጋግር አጠቃለይ የማክሮ ኢኮኖሚ ክለሳ ሒደት ውስጥ ነን›› ማለታቸውንም ሚንስቴሩ አሳውቋል።
ኢትዮጵያ በቅርቡ የአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነትን ማጽደቋም መንግሥት የምጣኑሀብት ዘርፉን ክፍት የማድርግ የቁርጠኝነቱ ማሳያ ነው ብለዋል።
ቅጽ 1 ቁጥር 21 የመጋቢት 21 ቀን 2011