የስኳር ልማት ፖሊሲ እየተዘጋጀ ነው

0
652

የስኳር ልማቱ የሚመራበት አዲስ ፖሊሲ እየተዘጋጀ መሆኑን የስኳር ኮርፖሬሽን ገለፀ።

የኮርፖሬሽኑ ተጠባባቂ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዋዩ ሮባ ኮርፖሬሽኑ ለኢዜአ እንዳሉት ኢትዮጵያ የስኳር ልማት የሚመራበት ፖሊሲ የላትም።
ፖሊሲ አገዳና ስኳር አምራች ፋብሪካዎች እንዲሁም ስኳር አከፋፋዮች የሚመሩበት አጠቃላይ አሰራርን የያዘ ይሆናል።

ለስኳር ምርት ግብአት የሚውል አገዳ ከአምራች ገበሬው ሲገዛ ገበሬው እንዳይጎዳና አምራቾች በውድ ዋጋ ገዝተው ተጠቃሚውን እንዳይጎዱ ፖሊሲው አቅጣጫ ያስቀምጣል።

በኢትዮጵያ ከተመረተው የስኳር ምርት ወደ ውጭ መላክ ያለበት ምርት መጠንና ከውጭ መግባት ያለበት ምን ያህል እንደሆነ በፖሊሲው ይካተታልም ተብሏል።

እስካሁን ኮርፖሬሽኑ የመንግሥት ስለሆነ ፖሊሲ አለመኖሩ የጎላ ተፅዕኖ አለማሳደሩን ግን ደግሞ በቀጣይ የውጭ ባለሀብቶች በዘርፉ ሲሰማሩ የፖሊሲው አለመኖር አሉታዊ ጫና ስለሚያሳድር ፖሊሲወ መዘጋጀቱ አስፈላጊ ይሆናል ተብሏል።

የፖሊሲው የመነሻ ሐሳብ ለገንዘብ ሚኒስቴር የተላከ ሲሆን፣ በቅርቡ ይጠናቀቃል ተብሎም ይጠበቃል።

ቅጽ 1 ቁጥር 21 የመጋቢት 21 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here