የናዝራዊትን ጉዳይ የሚከታተል ቡድን ተዋቀረ

0
483

በቻይና ዕፅ ይዛ ተገኝታለች በሚል ተጠርጥራ በእስር ቤት የምትገኘውን የናዝራዊት አበራ ጉዳይ የሚከታተል ቡድን ሥራ መጀመሩን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ።

ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ያላትን የኹለትዮሽ የህግ ማዕቀፍ፣ ዓለም አቀፍ የሕግ ስምምነቶችና ከአገሪቱ ጋር ያለውን መልካም ግንኙነት በመጠቀም ጉዳዩን የሚከታተል ቡድን ማዋቀሩን ዐቃቤ ህግ አስታውቋል።

የቡድኑ ኃላፊነት በቻይና በተጠርጣዋ ናዝራዊት ላይ የሚካሔደውን ምርመራ እና በኢትዮጵያ ከድርጊቱ አፈፃፀም ጋር ያለውን ሒደት መከታተል ነው ተብሏል።

ቤተሰቦቿ ለተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን አውታሮች ቅሬታቸውን ሲያቀርቡ ናዝራዊት የግንባታ ማጠናቀቂያ ግብዓቶችን የገበያ ዋጋ ለማጥናት ቻይና መሔዷን በመግለፅ አብሮ አደጓ ስምረት ካሳይ ቻና እንድታደርስላት በላከቻት አምስት ‹‹ሻምፖ›› ምክንያት መያዟን ያነሳሉ።

በቤጂንግ አየር ማረፊያ የናዝራዊት ሻንጣ ሲፈተሸ ሻምፖ ናቸው በተባሉት ምርቶች ውስጥ ኮኬን የተሰኘው አደንዛዥ ዕፅ ተቀላቅሎባቸው መገኘቱ ለእስር እንደዳረጋትም ተነግሯል።

በቻይና ሕግ ኮኬን እስከ ሞት ቅጣት የሚያርስ ቢሆን እስካሁን በቁጥጥር ስር ውላ በእስር ቤት ውስት ከመገኘቷ ውጭ ገና ክስም እንዳልተመሰረተባት ታውቋል።
ከሰሞኑ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ነብያት ጌታቸው ሲናገሩ ናዝራዊት ላይ ክስ አለመስረቱንና በየማኅበራዊ አውታሮች የሚሰራጩት የተፈርዶባታልና ሌሎች የሐሰት መረጃዎች ተገቢ አለመሆናቸውን መናገራቸው ይታወሳል።

ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲን እከተላለሁ ያለው የውጭ ጉዳይ ሚንስቴርም የናዝራዊትን ጉዳይ እየተከታለው ከቻይና መንግሥትም ጋር በቅርበት እየተነጋገረ መሆኑንም አክለዋል።
በቻይና ዕፅ ይዛ ተገኝታለች በሚል ተጠርጥራ በሕግ ጥላ ስር የምትኘው ናዝራዊት በሲቪል ምኅንድስና የተመረቀችና በጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ዘርፍ ስትሰራ የነበረች መሆኗን ቤተሰቦቿ ተናግረዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 21 የመጋቢት 21 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here