በትግራይ በ7 ቢሊዮን ብር የኬሚካል ፋብሪካ እየተገነባ ነው

0
610

በ7 ቢሊዮን ብር ወጪ 420 ሄክታር ላይ የሚያርፈው ደጀና ኬሚካል ኢንድስትሪ በትግራይ ክልል መቀሌ አቅራቢያ እየተገነባ ነው፡፡

በቻይናው ሲኢሲ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የሚገነባው ፋብሪካው የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ በሕይወት እያሉ የታቀደ ነው፡፡

ደጀና ኬሚካል ኢንዱስትሪ 10 የተለያዩ ኬሚካሎችን ያመርታል የተባለ ሲሆን ስድስት ኬሚካሎችን በዋናነት ለገበያ ያቀርባል ተብሏል፡፡

ፒቪሲ (ፖሊቪኒል ክሎራይድ) የሚሰኘው ትልቁ የኬሚካል ምርት ሲሆን ኮስቲክ ሶዳ፣ ሶዲየም ባይ ካርቦኔት እና ሌሎችንም ያመርታል፡፡

ኖራና ጨው ፋብሪካው በግብዓትነት ከሚጠቀማቸው ጥሬ እቃዎች መካከል ናቸው። ደጀና ኬሚካል ኢንዱስትሪ 50 በመቶ ግንባታው የተጠናቀቀ ሲሆን ሚያዝያ 2012 ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ቅጽ 1 ቁጥር 22 የመጋቢት 28 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here