ምስራቅ ሀረርጌ 62 ሺሕ ተፈናቃዮችን ሊመልስ ነው

0
192

የምስራቅ ሀረርጌ ዞን አስተዳደር ባለፈው ሐምሌና ነሐሴ በሱማሌ በነበረው አለመረጋጋት ተፈናቅለው ወደ ባቢሌ የሔዱ ከ62 ሺሕ በላይ ተፈናቃዮችን ወደ ቀደመ የመኖሪያ ቀያቸው ለመመለስ አቅዷል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የሰብኣዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤትን ጠቅሶ ሪሊፍ ዌብ ያወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው የዞኑ አስተዳደር ተፈናቅለው ወደ ባቢሌ የሔዱትን ኢትዮጵያዊያን ለመመለስ እየሰራ ነው፡፡ እንዲመለሱ ከታቀዱት 62 ሺሕ ተፈናቃች ውስጥ አብዛኖቹ በሐምሌ 2010 መጨረሻ ቀናት በጅግጂጋ በነበረውና እሱን ተከትለው በተንሰራፉት የሱማሌ ክልል ከተሞች ሁከት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ናቸው፡፡

በተያያዘ ረቡዕ የወጣ ሪፖርት እንደሚያሳያው በዓለም ዐቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት (አይኦኤም) የቅርብ መረጃ ኢትዮጵያ ሦስት ነጥብ 19 ሚሊዮን የአገር ውስጥ ተፈናቃዮችና ድጋፍ የሚሹ ተመላሾች አሏት፡፡ ተመላሽ የሚባሉትም ከተፈናቀሉ በኋላ ነገሮች ተረጋግተው ወደ ቀወያቸው ሔደው የሚቋቋሙትን ነው፡፡

ከተፈናቃዮቹ መካከል 30 በመቶዎቹ አስቸኳይ ድጋፍ ሊደርስላቸው የሚገቡና በአደጋ ውስጥ የሚገኙ ናቸው፡፡ ከአጠቃላይ ተፈናቃዮቹ መካከል 47 በመቶዎቹ በኦሮሚያ፣ 32 በመቶዎቹ በሱማሌ እንዲሁም 13 በመቶዎቹ በደቡብ ክልል እንደሚገኙም ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡

ቅጽ 1 ቁጥር 22 የመጋቢት 28 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here