የቦይንግ አውሮፕላን አምራች ብቃት እንዲፈተሽ ተጠየቀ

0
573

ቦይንግ አውሮፕላንን የሚያመርተው ኩባንያ በዓለም ዐቀፍ የአቬሽን ተቋማት ዳግም ብቃቱ አንዲፈተሽና እንዲረጋገጥ የምርመራ ቡድን ጠየቀ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ ከደረሰበት ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ጋር በተያያዘ እየተካሔደ ያለውን ምርመራ የመጀመሪያ ሪፖርት ያቀረበው ቡድኑ ካቀረባቸው ኹለት ምክረ ሀሳቦች አንዱ የአምራቹ ብቃት ዳግም ይረጋገጥ የሚለ ነው፡፡ በተጨማሪም ተደጋጋሚ የሆነ የአውሮፕላን አፍንጫ የመድፈቅ አደጋ የተለየ በመሆኑም አምራቹ ፍተሻ እንዲያደርግ ጠይቋል፡፡

በትራንስፖርት ሚንስቴር የሚመራው የምርመራ ቡድን በሰጠው መግለጫ የመጀመሪያ ግኝቶቹን ይፋ አድርጓል፡፡ ይኸውም አውሮፕላኑ የፀና ሰርተፍኬት እንዳለው፣ አብራሪዎቹ ብቃት እንዳላቸው፣

አውሮፕላኑ ሲነሳ በትክክለኛው መስመር መጓዝ የሚያስችለው ሁኔታ ላይ እንደነበር እና አብራሪዎቹ አውሮፕላኑን ለመቆጣጠር በአምራቹ የተሰጠውን ቅደም ተከተል ተከትለው ቢሰሩም መቆጣጠር አለመቻላቸውን የሚመለከት ነው፡፡

የትራንስፖርት ሚኒስቴር የሚያስተባብረው የምርመራ ቡድን በ1 ዓመት ዋናውን የምርመራ ሥራ አድርጎ ውጤቱን ይፋ አደርጋለሁ ብሏል።አውሮፕላኑን ከውጭ የመታው ነገር አለወይ ተብሎ የተጠየቀው ቡድኑ በምርመራ አለማግኘቱን አሳውቋል፡፡

ቅጽ 1 ቁጥር 22 የመጋቢት 28 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here