ብሔራዊ ባንክ 12 ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር ሰበሰበ

0
608

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በ2011 በጀት ዓመት ስምንት ወራት ውስጥ ለመሰብሰብ ካቀደው ዘጠኝ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በ32 በመቶ እቅዱን በማሳደግ 12 ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን አስታወቀ።

ከውጭ ምንዛሪ ‹‹ሪቫሉዌሽን›› የተገኘው ትርፍ እንዲሁም ከወለድና ከአገልግሎት ክፍያ ጋር በተያያዘ የተሰበሰበው ገቢ ከታቀደው በላይ መሆኑ ለባንኩ የገቢ እድገት ከፍ ማለት በዋና ምክንያትነት ተጠቅሷል።

በሌላ በኩል ደግሞ ለብር ኖቶች ሕትመትና ለወለድ የተፈፀመው ክፍያ ከተያዘው ዕቅድ ያነሰ ነው ተብሏል፡፡ ይህም ለበጀት ዓመቱ ስምንት ወራት የታቀደው መደበኛ ወጪ ሦስት ነጥብ ቢሊዮን ብር የነበረ ቢሆን መጠነኛ የወጪ ቅናሽ አድርጎ ሦስት ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር ወጪ ተደርጓል።

ቅጽ 1 ቁጥር 22 የመጋቢት 28 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here