20,440 ደረቅ ጭነት ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ያለ ሥራ በመቆማቸው 230 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ታጥቷል

0
695

እንደ ጉምሩክ ኮሚሽንና መንገዶች ባለሥልጣን ያሉ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ባለመሥራታቸው ምክንያት 20 ሺሕ 440 ድንበር ተሻጋሪ ደረቅ ጭነት ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ያለ አግባብ እንደሚቆሙና ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ብቻ 230 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ አገሪቷ እንዳጣች የኢትዮጵያ ትራንስፖርት ባለሥልጣን ገለፀ።

የመፈተሻ ጣቢያዎች ውስጥ ለሚሠሩ ሠራተኞች 24 ሰዓት እንዲሠሩ የሥራ ሰዓት ማሻሻያ ከተደረገ በኋላ በደቡብ፣ በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች ላይ መሻሻል ቢታይም፥ በሚፈለገው መጠን ባለመሆኑ ዋጋ እያስከፈሉ ነው ሲል ባለሥልጣኑ ባለፈው ማክሰኞ፣ መጋቢት 24 በተዘጋጀ የውይይት መድረክ ወቅት ገልጿል።

የዲመሬጅ አዋጅ መመሪያ መሠረት በቂ ዝግጅት አለማድረግ፣ መጋዘኖች ዝግጁ አለመሆን፣ ቴክኖሎጂ መር አሰራሮች ተግባራዊ አለመሆናቸው፣ የመጋዘን ሠራተኞች ውስንነትና የኃላፊነት መደራረብ ተሽከርካሪዎች በተፈለገው ፍጥነት እንዳይሠሩ ተግዳሮት እንደሆነባቸው ተግልጿል።

በተለይም በዋና ዋና የአገር ውስጥ ደረቅ ወደቦች በቃሊቲ፣ በድሬዳዋ፣ በአዳማ፣ በኮምቦልቻ፣ በሞጆ እስከ 300 በላይ የጭነት ማመላለሻ ተሸከርካሪዎች እሁድ መሥራት ባለመቻላቸው እና ሥራ ላይ ሲሆኑ የሚንቀሳቀሱበት ሰዓት ተመሳሳይ በመሆኑ ከትራፊክ መጨናነቅ ጋር በተያያዘም ችግር እየፈጠሩ ነው ተብሏል፡፡

ቅጽ 1 ቁጥር 22 የመጋቢት 28 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here