መዝገብ

Author: ህድአት አማረ

አወዛጋቢው የባሕር ዳር ከተማ የደረቅ ቆሻሻ ማከማቻ ግንባታ ተሰረዘ

ከ6 ዓመታት በፊት በባሕር ዳር ከተማ በ10 ሺሕ ሔክታር መሬት ላይ ሊገነባ ታቅዶ የነበረው እና በአርሶ አደሮች ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞት የነበረው የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ፕሮጀክት ተሰረዘ። የእርሻ መሬታቸውን በተደጋጋሚ ለተለያዩ የልማት ሥራዎች እየተወሰደባቸው ምክንያት በማድረግ የቀረውን ቦታቸውን ለቆሻሻ ማስወገጃ ፕሮጀክተቱ…

እንቦጭን ጥቅም ላይ ለማዋል ሦስት ዓመት የሚፈጅ ጥናት ሊካሔድ ነው

የውሃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር ከኦሲፒ አፍሪካ ጋር ባደረገው ስምምነት እንቦጭን ወደ ማዳበሪያነት ለመቀየር የሚያስችል ጥናት ማካሔድ በሐምሌ 2011 የሚጀምር ሲሆን ጥናቱም በሦስት ዓመት ውስጥ የሚጠናቀቅ መሆኑ ታውቋል። በባሕር ዳር ጣና ሐይቅ ላይ ምርምር እንደሚደረግ የኦሲፒ አፍሪካ ተወካይ ሰላምይሁን ኪዳኑ (ዶ/ር)…

ብሔራዊ ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት መመሪያ እያሻሻለ ነው

ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት በመደበኛው ባንክ ውስጥ በሚገኙ መስኮቶች ውስጥ ብቻ እንዲገደብ ያደረገው መመሪያ እየተሻሻለ በመሆኑ በመመስረት ላይ ለሚገኙ የወለድ ነጻ ባንኮች ሕጋዊ መሰረት ይሰጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ታወቀ። ዘምዘም ባንክ ከዓመታት በፊት ወደ ሥራ ለመግባት ሲሞክር በብሔራዊ ባንክ የወጣው ከልካይ…

400 ብር የገባው የሲሚንቶ ዋጋ መመርመር ተጀመረ

በኢትዮጵያ የተከሰተውን የኀይል መቆራረጥ ተከትሎ የሲሚንቶ አቅርቦት በመቀነሱ በገበያ ላይ የ42 ነጥብ 8 በመቶ የዋጋ ጭማሪ በመታየቱ ምክንያቱ ምጣኔ ሀብታዊ መሆን አለመሆኑን የንግድ ውድድር እና የሸማቾች መብት ጥበቃ ባለሥልጣን ምርመራ ማካሔድ ጀመረ። የባለሥልጣኑ የምርመራ ቡድን አምስት ዋና ዋና የሲሚንቶ አምራቾችን…

የመኪና መለዋወጫ ዋጋ መናር የትራስፖርት እጥረት ፈጥሯል

ላለፉት ዐሥራ አምስት ዓመታት በሚኒባስ ታክሲ ሹፌርነት የሚተዳደሩት አየነው ንጋቱ ሰባት ልጆቻውን ጨምሮ ቤተሰቡን ለሚያስተዳድሩባት የመኪና መለዋወጨ ፍለጋ ከቄራ፣ ቡልጋሪያ ከዛም ጨርቆስ በመዟዟር ይባዝናሉ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየናረ የመጣው የመለዋወጫ ዋጋ ለሥራቸቸው ተግዳሮት እንደሆነባቸው የሚናገሩት አየነው ከአንድ ወር በፊት 80…

ኤጀንሲው ለማረሚያ ቤቶች በ5 ሚልዮን ብር መጻሕፍት ሊገዛ ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ኤጀንሲ በክረምት የንባብ ባሕልን ለማዳበር በተያዘው መርሃ ግብር መሰረት “በመጽሐፍ እንታረም” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ፣ ሸዋሮቢት፣ ድሬ ዳዋ፣ ባሌ ሮቤና ወላይታ ማረሚያ ቤቶች ውስጥ ለሚገኙ ታራሚዎች ልገሳ ለማድረግ ግዢ ሊፈፅም ነው። በማረሚያ ቤቶች…

በአዲስ አበባ የደራው የሐሰተኛ ሰነዶች ገበያ

በአንድ የማስታወቂያ ድርጅት ውስጥ ባልደረባ ለሆነችው ለ22 ዓመቷ ሜላት አስመላሽ (ሥሟ የተቀየረ) ዳጎስ ያለ ክፍያ የሚያስገኝ የማስታወቂያ ሥራ ማግኘቷን እንዲሁ በቀላሉ የምታልፈው አጋጣሚ አልነበረም። ለወራት በኮንትራት በምትሠራበት የማስታወቂ ድርጅት ሥራውን ሊሰጣት መስማማቱ መልካም ዜና ቢሆንም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(‘ቲን’) ከሌላት…

በሞጆ ደረቅ ወደብ 1 ሺሕ 345 ኮንቴይነሮች ለጨረታ ሊቀርቡ ነው

በጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ደረቅ ወደብ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ከስልሳ ቀናት በላይ ሳይነሱ የቆዩ ምግብ ነክ ዕቃዎችና የሕክምና መገልገያ ቁሳቁሶች የያዙ 1 ሺሕ 345 ኮንቴነሮችን ለጨረታ ሊያቀርብ እንደሆነ አስታወቀ። አስመጪዎች በተለይም የሚጣልባቸውን ቀረጥ ለመክፈል ባለመቻለቸው እና የባንክ ሰነድ ማስተላለፍ ላይ የሚደርሱ…

ፓርላማው ዳኛ አየለ ወደ ሥራ ገበታቸው እንዲመለሱ ወሰነ

ከጥቅምት 2011 ጀምሮ የፌደራል ዳኞች አስተዳድር ጉባኤ በጣለባቸው ውሳኔ መሰረት ከደመወዝ እና ከሥራ ታግደው የቆዩት የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ አየለ ዲቦ ወደ ሥራ ገበታቸው እንዲመለሱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወሰነ። ሰኞ፣ ግንቦት 12 በተደረገው መደበኛ ጉባኤ ላይ በሕግና ፍትሕ፣…

1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር የተቆረጠለት መሬት ለራስ ቴአትር ተሰጠ

በከተማው አስተዳደር ለቴአትር ቤቱ ግንባታ 4 ሺሕ 500 ካሬ እንዲሰጥ ወስኗል በተለምዶ አሜሪካ ግቢ ተብሎ የሚጠራው ቦታ ለስድስት ዓመታት ግንባታው ለተንጓተተው የራስ ቴአትር ግንባታ እንዲደረግበት በተለዋጭነት ተሰጠ። በአዲስ አበባ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ባሕል ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ዳይሬክተር ሜሮን ተሻለ…

ጊዜ ያለፈባቸው የምግብ ምርቶች ከሸማቾች ማኅበራት ተያዙ

የአራዳ ክፍለ ከተማ የምግብና መድኀኒት ቁጥጥር ጽሕፈት ቤት ጊዜያቸው ያለፈባቸው በርካታ የምግብ ምርቶችን ከሸማች ማኅበራት መያዙን አስታወቀ። የኑሮ ውድነትን ለመቋቋም በማሰብ መንግሥት ሸማቾችን በማደራጅት በተመጣጣኝ ዋጋ እቃዎችን በጀምላ እንዲያገኙ ይደረጋል። ጊዜያቸው ያለፈባቸውና ከ285 ሺሕ ብር በላይ የሚገመቱ በአቀማመጥ ችግር የተበላሹ…

በአዋሽ ፍተሻ ጣቢያ መፈተሻ ማሽን ብልሽት ገጥሞታል

በአዋሽ የፍተሻ ጣቢያ በጨረር የመፈተሻ ማሽን (የኤሌክትሮኒክስ ካርጎ ስካኒንግ) ለኹለት ወራት ተበላሽቶ በመቆሙ የአገሪቱ ወሳኝ መግቢያ እና መውጫ የሆነው በዚህ ጣቢያ ሥጋት ተፈጥሯል። ማሽኑን በገጠመው የቻይና ድርጅት እና በገቢዎች ሚኒስቴር መካከል በተፈጠረ ያለመግባባት ማሽኖቹ ሳይጠገኑ መቆየታቸውም ታውቋል። በቅድሚያ የተበላሸው ማሽኑን…

የመርከብ ባለሞያዎችን የሚያሰለጥነው ድርጅት ሕጋዊነት ጥያቄ አስነሳ

ድርጅቱ የተመዘገበ ቢሆንም ከግብር እና ከሠራተኞች ሰብኣዊ መብቶች አያያዝ ጋር ጥያቄ ተነስቶበታል የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግን ጨምሮ ለ6 ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ የኢትዮጵያ ማሪታይም ትሬዲንግ ኢንስቲትዩት ፈቃድ ሳይኖረው ከ2002 ጀምሮ ተማሪዎችን በራሱ አሠልጥኖና አስመርቆ…

በትግራይ ክልል ጊዜአቸው ያለፈባቸው የፀረ አረም ማጥፊያ መድሃኒቶች ለገበሬዎች ሊሰጥ ነው

በትግራይ ክልል 1 ሺ 82 ሊትር ጊዜ ያለፈባቸው የፀረ አረም መድሃኒቶች ክምችት ውስጥ 345ቱ የጥቅም ጊዜአቸው ቢያልፍም ለገበሬዎች እንደሚሰጥ የክልሉ የሕብረት ስራ ኤጀንሲ አስታወቀ። እነዚህ መድሃኒቶች ጊዜአቸው እንዳለፈባቸው ለግብርና ሚኒስቴር ጥቆማ ሰጥጠናል ያሉት የኤጀንሲው የአዝርዕት ግብዓት አቅርቦት ባለሙያ የሆኑት አለባቸው…

የሥጋ ነገር

በተለምዶ ቄራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው አንድነት ሥጋ ቤት በተቆጣጣሪነት የምታገለግለው ምዕራፍ ትዕግስቱ የሥጋ ተመጋቢ ደንበኞች የሥጋ ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ትናገራለች። በተለይም በቡድን የሚመጡ ጓደኛሞች በጋራ እስከ አራት ኪሎ ጥሬ ሥጋ በአንድ ማዕድ መመገብ እንደተለመደ ታስረዳለች። በአዲስ…

የፌዴራል ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ 540 ሚሊዮን ብር ከሰረ

• ማቀነባበሪያው በ2007 ሥራውን የጀመረ ሲሆን በዓመት 500 ሺሕ ኩንታል የማምረት አቅም ነበረው የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ባለፉት ሦስት ዓመታት በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች ለማደበሪያ ማቀነባበሪያ ላስገነባቸው ፋብሪካዎች ግብዓት የሚሆን ጥሬ ዕቃ ከውጭ አገር ማስገባቱን ተከትሎ በአምስት የኢትዮጵያ ክልሎች ላይ አራት…

‘አፍሪ ሄልዝ’ ቴሌቪዥን ጣቢያ በከፊል ተሸጠ

በሕክምና፣ በመገናኛ ብዙኃን አውታር ባለሙያዎች እና በባለሀብቶች በ40 ሚሊዮን ብር የተቋቋመው ʻአፍሪ ሄልዝʼ የቴሌቪዥን ጣቢያ 50 በመቶ ድርሻው ለሐበሻ ዊክሊ ፕሮሞሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ተሸጠ። አፍሪ ሄልዝ ቴሌቪዥን ሲቋቋም ዋና ዓላማ አድርጎ የተነሳው ሰዎች የራሳቸውን ጤና በራሳቸው መንከባከብ እንዲችሉ…

በአዲስ አበባ ለሞተር ሳይክል ሰሌዳ መስጠት ቆሟል

በአዲስ አበባ ለሞተር ሳይክሎች ሰሌዳ መሰጠት መቆሙን የፌደራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን የውስጥ ምንጮች ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። በአዲስ አበባ 24 ሺሕ የሚያህሉ ሞተር ሳይክሎች የሚገኙ ሲሆን፣ ከነዚህ ውስጥ 16 ሺሕ የሚሆኑት የክልል ሰሌዳ ያላቸው መሆኑም ታውቋል። እነዚህ ሞተር ሳይክሎች በጦር ኃይሎች፣ አየር…

‘ነብይ ዤሮ’

ዕለቱ እሁድ፣ ቦታው ባለግርማ ሞገሱ የአዲስ  አበባ ቴአትርና ባሀል አዳራሽ፣ ሰዓቱ ስምንት ተኩል፤ ቴአትር በተጠማ ተመልካች አዳራሹ ጢም ብሎ ሞልቷል። መብራቶች ጠፍተው ለአፍታ አዳራሹ ጨልሟል፤ ወዲያውም የመድረኩ መጋረጃ ተከፈተ። መቼቱን የባሕር ዳርቻ አድርጎ የሚጀምረው ተውኔት ዋናው ገጸ ባህሪይ ደማቅ አረንጓዴ…

የዲቴል ጋላፊ መንገድ በመበላሸቱ በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ መሆኑ ታወቀ

በጁቡቲ መንግሥት የሚተዳደረው የዲቴል ጋላፊ መንገድ በመበላሸቱ በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ መሆኑንና ኮንቴነር ለጫኑ ተሽከርካሪዎችም የአደጋ መንስኤ እየሆነ መሆኑ ታወቀ። ይህ መንገድ ብልሽት ካጋጠመው ከ3 ዓመት በላይ የሆነው ሲሆን ወደ ጉድጓድነት በመቀየሩ ኮንቴነር የጫኑ መኪኖች የመገልበጥ አደጋ እየገጠማቸው መሆኑንና…

አባይ 102.9 ኤፍ ኤም ኪሳራ ማወጁን ተከትሎ በሀራጅ ሊሸጥ ነው

አባይ ኤፍ ኤም የሬዲዮ ጣቢያ በአሁኑ ጊዜ የከሰረና ሥራ ለመቀጠል አማራጭ የገንዘብ ምንጭ ሊያገኝ ያልቻለ በመሆኑ በንግድ ሕግ መሠረት ኪሳራን በማወጅ ለመዝጋት ሒደት ላይ እንደሆነና በደረሰበት ኪሳራ ለሠራተኞች ደሞዝ መክፈል ባለመቻሉ ፍርድ ቤት ሚያዝያ 8 የሐራጅ ሽያጭ ተመን እንደሚያወጣ ተገለፀ።…

ድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች ጥቃትና ዘረፋ እየደረሰባቸው ነው

የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ማኅበራት በመዳረሻ ቦታዎች ላይ ጥቃትና ዘረፋ እየደረሰባቸው እንደሆነ የፌደራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን መጋቢት 24 ባዘጋጀው የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ላይ አስታወቁ። በመድረኩ ተሳታፊ የነበሩ የማኅበራቱ ተወካዮች በአንዳንድ ክልል ውስጥ ያሉ የጎበዝ አለቆች አላሠራ እንዳሏቸው፣ ያለአግባብ ገንዘብ እንዲከፍሉ እንደሚደረጉ፣…

20,440 ደረቅ ጭነት ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ያለ ሥራ በመቆማቸው 230 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ታጥቷል

እንደ ጉምሩክ ኮሚሽንና መንገዶች ባለሥልጣን ያሉ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ባለመሥራታቸው ምክንያት 20 ሺሕ 440 ድንበር ተሻጋሪ ደረቅ ጭነት ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ያለ አግባብ እንደሚቆሙና ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ብቻ 230 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ አገሪቷ እንዳጣች የኢትዮጵያ ትራንስፖርት ባለሥልጣን ገለፀ። የመፈተሻ…

የመሣሪያ እጥረት አላሰራ አለኝ ያለው ኢንስቲትዩት 14 ሚሊዮን ብር ተመላሽ አደረገ

በቤተ ሙከራ ዕቃዎች እጥረት የሚጠበቅበትን ተግባር ማከናወን እንደተሳነው የገለፀው የኢትዮጵያ ባዮቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት 15 በመቶ የሚሆን በጀቱን ተመላሽ እንዳደረገ አሳወቀ። ኢንስቲትዩቱ በቤተ ሙከራ መሣሪያዎች እጥረት ምክንያት ለመሥራት መቸገሩ የተገለፀ ሲሆን፣ በጀቱ በመኖሩ ለመግዛት ጥረት ቢደረግም ግዢ ለመፈፀም በሚወስደው ረዥም ጊዜ ምክንያት…

3497 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ቅሬታ አስገቡ

3497 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ከቦታ አላግባብ መፈናቀል፣ የደሞዝ ጭማሪ፣ ዕድገት የሥራ ድርሻና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች ካለማግኘት ጋር በተያያዘ ቅሬታዎች እንዳቀረቡ የድርጅቱ የሠራተኞች ማኅበር ለአዲስ ማለዳ ገለፀ። ከነዚህም መካከል 2722 የሚሆኑት የድርጅቱ ሠራተኞች ዕድገት ልናገኝ ይገባል በማለት ቅሬታ ሲያቀርቡ 700…

በአፋር ከ300 በላይ ሰዎች በወረርሽኝ ምክንያት አደጋ ላይ ወድቀዋል

በአፋር፣ አዳል ወረዳ ʻኤደስ ኤጂፕታይʼ በተባለ ትንኝ አማካይነት በየቀኑ 20 ሰዎች የችኩንጉኒያ በሽታ እንደሚጠቁና እስካሁንም ከ300 በላይ ሰዎች በወረርሽኙ ምክንያት ሕይወታቸው አደጋ ውስጥ መግባቱ ተነገረ። ወረርሽኙ እንደተከሰተ ከታወቀበት የካቲት 2011 ጀምሮ በአስቸኳይ የሕክምና ቡድን ወደ ሥፍራው እንደተላከ የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና…

የትግራይ ክልል የቤት እጥረት ለመቅረፍ 100 ሄክታር መሬት ለነዋሪዎች አዘጋጀ

በትግራይ ክልል የቤት እጥረት ለመቅረፍ ለግለሰቦችና ማኅበራት 100 ሄክታር መሬት መዘጋጀቱን መስተዳደሩ አስታወቀ። በክልሉ ለ500 ማኅበራት የሚሆነ መሬት የተዘጋጀ ሲሆን ለአንድ ሰው 70 ካሬ ለመስጠት ምዝገባ መጀመሩን ክልሉ ይፋ አድርጓል። የቤት እጥረትን ለመቅረፍ በማኅበር ለተደራጁ ነዋሪዎች መሬት መስጠት የተጀመረው በ2009…

ብሔራዊ ሜቲዮሮሎጂ በኦሮሚያና ሶማሌ በዝናብ እጥረት ምክንያት ድርቅ ሊያጋጥም እንደሚችል አስጠነቀቀ

ብሔራዊ ሜቲዮሮሎጂ ኤጀንሲ ቦረናን ጨምሮ በኦሮሚያና ሶማሌ ብሔራዊ ክልሎች አዋሳኝ ከተሞች የዝናብ እጥረት ሊያጋጥማቸውና ለድርቅ ሊጋለጡ ይችላሉ ሲል ሥጋቱን ገለፀ። በእነዚህ አካባቢዎች ባለፈው ዓመት ከመጠን ያለፈ ዝናብ የነበረና ሰብል አበላሽቶ የነበረ ሲሆን በዚህ ዓመት የዝናብ እጥረት ሊከሰት እንደሚችል ፍንጭ መገኘቱ…

የገንዘብ እጥረትያጋጠመው ዳሽን ቢራ 400 ሚልዮን ብር ከንግድ ባንክ ተበደረ

ዳሽን ቢራ አክስዮን ማኅበር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከዚህ ቀደም ለወሰዳቸው ቆርኪ ፋብሪካና ብቅል ግብዓቶች ክፍያ ለመፈፀም 400 ሚሊየን ብር ከንግድ ባንክ እንደተበደረ ምንጮች ለአዲስ ማለዳ ገለፁ። በኢትዮጵያ የቢራ ኢንዱስትሪ በአቅም ደረጃ ከሔኒከንና ቢጂአይ ቀጥሎ ሦስተኛን ደረጃ የያዘው ዳሽን ቢራ በአገሪቷ…

በ3 ቢሊየን ብር የገበያ ማዕከል እገነባለው ያለው ድርጅት ውጥረት ውስጥ ገብቷል

• ድርጅቱ 28 ሚሊዮን ብር ከ3500 ባለአክሲዮች ሰብሰቧል የዛሬ ኹለት ዓመት ገደማ በ3 ቢሊየን ብር የገበያ ማዕከል እገነባለው ብሎ እስካሁን ወደ 28 ሚሊየን ከተለያዩ ባለሀብቶች የሰበሰበው የሕዳሴ አክስዮን ማኅበር ከአዲስ አበባ መስተዳድር ምንም ዓይነት ይሁንታ አለማግኘቱና የግንባታውን ተፈፃሚነቱ አጠራጣሪ ደረጃ…

This site is protected by wp-copyrightpro.com