የአሜሪካ መንግሥት ፍትሕ ለተሰኘው እና የፌደራሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግና የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለሚያካሂዷቸው ገለልተኛ የፍትሕ አሰጣጥ ማሻሻያ ሥራዎች መደገፊያ 112 ሚሊዮን ብር ለግሷል።
በኹለት ዓመት ለሚተገበረው ይህ ፕሮጀክት የተሰጠው ገንዘብ የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬቶች፣ በስሩ ለሚገኙ ኤጀንሲዎች እና ላቋቋማቸው የአማካሪ ጉባኤ እና ሴክሪታሪያቱ ለሚሰጡ የቴክኒክ ድጋፎች የሚውል ነው።
የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም የንግድ ችሎትን ለማጠናከር እንዲሁም የፌደራል የተለያዩ ዘርፍ ችሎቶች የሕግን ማእቀፎችን ለማሻሻል ለሚሰራቸው ተግባራት ድጋፉን ይጠቀምበታል ተብሏል።
አሜሪካ ባለፉት አራት ዓመታት በኢትዮጵያ ለተለያዩ ድጋፎች ከአራት ቢሊዮን ዶላር በላይ መለገሷ ተገልጿል።
ቅጽ 1 ቁጥር 23 ሚያዚያ 5 ቀን 2011