በቁጥጥር ስር ዋለች!

0
574

አደገኛ ዕፅ በማዘዋወር ወንጀል ተጠርጥራ በቻይና እስር ቤት የምተገኘው ኢትጵያዊቷ ናዝራዊት አበራ፣ በሀገረ ቻይና ይህ መሰሉ ወንጀል አስከፊ ፍርድን ከማስከተሉ ጋር ተያይዞ የብዙዎችን ቀልብ በመሳብ የኢትጵያ መንግሥት ነገሩን በዲፕሎማሲዊ መንገድ እንዲፈታው ከብዙዎች ሲጠየቅ መሰንበቱ ይታወሳል፡፡ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴርና የፌደራሉ ጠቅላ ዐቃቤ ሕግም ስለ ናዝራዊት ሲጠየቁ መንግስት በትኩረት እየተከታለው መሆኑን፣ ለዚሁ ተግባር የሚሰራ መቋቋሙን እንዲሁም የኢትዮጵያ መንግሥት የደራጀው ቡድን ከአንድም ኹለት ሦስቴ ናዝራዊት በታሰረችበት ቦታ ተገኝቶ ተጠርጣዋን መጠየቁን ሲገልፁ ሰንብተዋል።

በሌላ በኩል የናዝራዊት ቤተሰቦች ልጃቸው ወደ ቻይና ያቀናችው የግንባታ እቃዎች ዋጋን ለማጥናት እንደሆነ በመጥቀስ በቻና የታሰረችው በጓደኛዋ መልዕክት እንደሆነ አብዝተው ሲወቅሱ ነበር፡፡ ይኸውም ጓደኛዋ ስምረት ካህሳይ አብራት ወደቻና ልትሔድ የነበረ ቢሆን በበረራዋ እለት ባጋጠማት ችግር መጓዝ እንደማትችል ገልፃ ሻምፖዎችን ቻይና ለሚቀበላት ሰው እንድታደርስላት በመጠየቋ ነው ባይ ናቸው፡፡

ናዝራዊት ቻይና ደርሳ ቦርሳዋን ስታስፈትሽ በሻምፖ እቃ የተሰጣት ኮኬይን ተባለው አደገኛ ዕፅ ሆኖ በመገኘቱ መታሰሯንም ቤተሰቦቿ ለመገናኘ ብዙኋን ሲናገሩ ነበር፡፡ በዚህም የረጅም ጊዜ ጓደኛዋ ቅርርባቸውን ተጠቅማ ለችግር እንደዳረገቻት በመግለፅ ሲወቅሱ ነበር።

ከሰሞኑ ታዲያ ለናዝራዊት ኮኬን የተሰኘውን አደንዛዥ እፅ ሰጥታለች በሚል የተጠረጠረችው ጓደኛዋ ከሌላ አንድ ግለሰብ ጋር በቁጥጥር ስር መዋሏን ፖሊስ ሲገልፅ በርካታ የመገናኛ ብዙኃን አውታሮች ዜና ያደረጉት ሲሆን አያሌ የፌስቡክ ተጠቃሚዎችም ጉዳዩን ሲቀባበሉት ሰንብተዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 23 ሚያዚያ 5 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here