ኮንትሮባንድንና ሕገ ወጥ ንግድን ለመቆጣጠር የተቋቋመው የጉምሩክ ፖሊስ ወደ ሥራ ገባ

0
779

ኮንትሮባንድን ለመከላከል በ44 ኬላዎች ላይ 660 የጉምሩክ ፖሊሶች ተመድበው ወደ ሥራ ገቡ። ቁጥጥሩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች አገር ውስጥ ከገቡ በኋላ የተከማቹበትና የሚሰራጩበት አካባቢዎች ላይም ጭምር ክትትል በማድረግ ችግሩን ከሥር መሰረቱ ለማድረቅ እየተሠራ እንደሆነ የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአሁኑ ወቅት በጥናት ላይ በመመስረት 50 በመቶ በሚሆኑት የመቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ላይ የጉምረክ ፖሊስ ወደ ሥራ የገባ ሲሆን በቀሪዎቹ ኬላዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ሥራ እንደሚገባ ይጠበቃል።

በስምምነቱ መሰረትም ተጠሪነቱ ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የሆነው የጉምሩክ ፖሊስ ከጉምሩክ ኮሚሽን ጋር በመሆን የሥራ ስምሪት የመስጠትና ሥራውን በጋራ የመገምገም አሰራር የሚከተል ሲሆን ለጉሙሩክ ኮሚሽን ትራንስፖረትን ጨምሮ ሌሎች የሎጂስቲክ ግብዓቶችን የሚያቀርብ መሆኑም ተነግሯል።

የጉምሩክ ኮሚሽን የለውጥ ሥራዎችን ከጀመረ ወዲህ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ሥር እንዳዋለ የሚታወስ ነው።

ቅጽ 1 ቁጥር 25 ሚያዚያ 19 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here