ሕገወጥ የማዕድን ንግድ በትግራይ ክልል መስፋፋቱ ታወቀ

0
573

ሚያዚያ 4/2011 የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተፈጥሮ ሀብት፣ የመስኖ እና የኢነርጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በትግራይ ክልል ጭላ ቀበሌ በመገኘት በደረጉት ምልከታ 60 በሚጠጉ ሞተር ሳይክሎች በመጠቀም የሕገወጥ የመዕድን ንግድ ሰንሰለት መፈጠሩን መመልከታቸውን አስታወቁ።

የሕገወጥ ንግዱ በአንዳንድ የአካባቢው ነዋሪዎች እና ሕጋዊ የማዕድን አውጪዎች ጭምር የሚደገፍ ነው ሲል ቋሚ ኮሚቴው ገልጿል። የቀበሌዋ የውሃ ዘርፍ ኀላፊ ግኡሽ ከዚህ ቀደም አራት ማኅበራት ለማአድን ሥራው ተሰማርተው የነበረ ሲሆን ነገር ግን ማዕድኑ በቋሚነት የማይገኝ በመሆኑ እንዲሁም ቁፋሮው አካባቢውን መልከዓ ምድር ያበላሻል በማለታቸው መቋረጡን ተናግረዋል። የክልሉ የውሃ ሀብት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኀላፊ መላኩ እስጢፋኖስ በጭላ አካባቢ በባሕላዊ መንገድ በመውጣት ላይ ያለው ሳፋየር የተባለው የከበረ ማዕድን ጥሩ ዋጋ ቢኖረውም ወደባንክ ባለመቅረቡ የተወሰኑ ወጣቶች ብቻ ተጠቃሚ መሆናቸው አግባባ አደለም ሲሉ መልስ ሰጥተዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 25 ሚያዚያ 19 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here