በአንድ ዓመት 1.3 ቢሊዮን ብር የሚገመት የኮንትሮባድ ዕቃ በቁጥጥር ስር ዋለ

0
441

በታክስ ማዕከላትና በጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ላይ በተደረገ ጥገናዊ ለውጥ በያዝነው የዘጠኝ ወር የበጀት አፈፃፀም 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃ በቁጥጥር ሥር እንዲውል ሆኗል።

በተደረገ ቁጥጥር ከተያዙት ውስጥ በርካታ ካሜራዎች፣ ስማርት ስልኮች፣ የተለያዩ የተሸከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎችና ሌሎች ዕቃዎች በፍተሻ ጣቢያዎች ለያዙ ችለዋል።

ከ219 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃ ጠቅላላ ግምታዊ ዋጋው 219,368,600 ብር የሆነ የተለያዩ የኮንትሮባንድ ዕቃ በዲፕሎማቲክ የቀረጥ ነፃ መብት ሽፋን ወደ አገር ሊገባ ሲል ቦሌ ዓለም ዐቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለመያዝ ተችሏል።

በቁጥጥር ሥር ከዋሉት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ውስጥ 118,440,000 ብር የሚገመተው ካኖን ካሜራዎች ሲሆኑ 52,362,200 ብር የሚገመተው የስማርት ስልኮች ስክሪኖች ናቸው። ቀሪው የተለያዩ የተሽከርካሪዎች መለዋወጫዎች፣ መድኀኒት፣ ፕሮጀክተር፣ የብር ጌጣጌጥ እና ልዩ ልዩ ኬብሎች ናቸው።

ቅጽ 1 ቁጥር 25 ሚያዚያ 19 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here