በሐዋሳ ሀይቅ የዓሣ ሀብት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል

0
778

በሐዋሳ በሕገወጥ የማጥመጃ መሣሪያዎች ማጥመድና ከሚፈቀደው መጠን በላይ ማስገር በስምጥ ሸለቆ አካባቢ በሚገኙ ሐይቆች የሚመረተው የዓሣ መጠን ተፅዕኖ እየከፋ መምጣቱ ተነገረ።

መመረት ያለበት ዓሣ ለምግብነት የደረሰ መሆን እያለበት አስጋሪዎቹ ከመመርያና ከሚፈቀደው ውጪ ማንኛውንም ዓሣ በዘፈቀደ እያሠገሩ እንደሚገኙና ለምግብነት የደረሱትን ብቻ ማስገር ሲገባቸው፣ ጫጩቶቹንም በማስገራቸው የምርቱ ቀጣይነት አደጋ ላይ ወደወቋል።

ለሐዋሳ ሀይቅ መበከል ምክንያት እየሆኑ ያሉት ከየቤቱ የሚወጡ ፍሳሾች ወደ ሀይቁ እንዲገቡ መደረጉን ለአዲስ ማለዳ የተናገሩት የሚኒስቴሩ ሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ጋሻው ደበላ፣ ከኢንዱስትሪዎች፣ ከጋራጅ፣ ከሆቴል፣ ከሕክምና ተቋማትና ከየመኖሪያ ቤቶች የሚለቀቁ ፍሳሾች ሀይቁን እየበከሉት እንደሚገኙ ተናግረዋል። እነዚህን ችግሮች ለማስቀረት ከሦስት ዓመት በፊት ዘመቻ ተጀምሮ የነበረ ቢሆንም መቀረፍ ያለበትን ያህል ግን አልተቀረፈም ብለዋል።

የችግሩ ተጠቂ የሆነው የሐዋሳ ሀይቅ በዓመት ማምረት የሚችለው የዓሣ መጠን 3 ሺሕ 100 ኩንታል ሲሆን፣ አስጋሪዎች ከመጠን በላይ በማስገር የማምረት አቅሙ በእጥፍ ቀንሷል። በዚህም ምክንያት አገሪቱ በዓሣ ሀብት የሚገባትን ጥቅም እያገኘች አለመሆኑን፣ የማምረት አቅሟም በዓመት 185 ሺሕ ኩንታል እንደሆነና እየተገኘ ያለው ግን 12 ሺሕ ኩንታል ምርት ብቻ መሆኑንም አክለዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 25 ሚያዚያ 19 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here