የቻይና መንግሥት የሸገርን ማስዋብ ፕሮጀክት የሚሸፍን ድጋፍ አደረገ

0
501

ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቻይና እያደረጉት ያለው ይፋዊ የሥራ ጉብኝት የአገሪቱን ፕሬዘዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋ ረቡዕ፣ ሚያዚያ 16 የተለያዩ ስምምነቶችን ፈርመዋል። ከስምምነቶቹም መካከል የሸገርን የማስዋብ ፕሮጀክትን የሚሸፍን የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ መንግሥታቸው ጥረት እየደረገ መሆኑንም ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪ ፕሬዘዳነቱ ኢትዮጵያ በ2018 ሊከፈሉ የደረሱ ብድሮችን መዘረዟን አስታውሰው ቻይና ሃገሪቱ እያደረገች ባለችው የለውጥ ሥራዎች ድጋፍ እንደምታደርግ ተናግረዋል። የኢትዮ ጂቡቲ የምድር ባቡር መንገድ ግንባታን አስመልክቶ ያሉ እዳዎችን በተመለከተ አዳዲስ ክለሳዎችን ለማደረግ መዘጋጀታቸውንም ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በበኩለቸው በአደንዛዥ እፅ ማዘዋወር ተጠርጥረው በቻይና ያለችውን ኢትዮጵያዊት በተመለከተም ለፕሬዘዳንቱ አንስተው መወያየታቸውም ተገልጿል። ጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ አምስት ሚሊዮን ብር የሚያወጡጣ የእራት ግብዣዎችን በማዘጋጀት የተለያዩ ባለሀብቶች ለፕሮጀክቱ ድጋፍ እንዲያደርጉ መጠየቃቸው ይታወሳል።

ቅጽ 1 ቁጥር 25 ሚያዚያ 19 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here