የቡርቃ ዝምታ መንታ ትርክቶች

0
630

ባሳለፍነው እሁድ ሚያዝያ 13፣ 2011 የኦሮሞ እና የአማራ ሕዝቦችን ትስስር ለማጠናከር በሚል ዓላማ በተዘጋጀ መድረክ ላይ በቅርቡ አለሙ ስሜን በመተካት የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዲፒ) ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሆነው የተሾሙት አዲሱ አረጋ የሰጡት አስተያየት ሰሞኑን መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል።

የአማራ እና ኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድሮች በተገኙበት በተዘጋጀው መድረክ ላይ የልሂቃን እና የፖለቲከኞች የሃሰት ትርክት የአማራ እና የኦሮሞ ሕዝብን ለመከፋፈል ጥረት አድርጓል ሲሉ አዲሱ ትችት አዘል ንግግር ሰንዝረው ነበር። ሁለቱን ሕዝቦች እንደ እሳት እና ጭድ አድርገው ልሂቃን እና ፖለቲከኞች የተዛባ መረጃ ያቀርቡ ነበር ያሉት አዲሱ ለአብነትም ‘የቡርቃ ዝምታ’ የተሰኘውን የተስፋዬ ገብረዓብን መጽሐፍ መጥቀስ ይቻላል’’ ሲሉ ተደምጠዋል።

ይሁን እንጂ፤ አዲሱ በተናገሩት አስተያየት የተነሳ በኦሮሚያ አንዳንድ ከተሞች ከፍተኛ ተቃውሞ ተስተውሏል። ይህንንም ተከትሎ፤ አዲሱ ለህዝቡ ይቅርታ ጠይቀዋል። በፌስቡክ ገጻቸው ላይም ‘’ ‘የቡርቃ ዝምታ’ መጽሐፍን በተመለከተ የሰጠሁት አስተያየት ብዙዎችን እንዳላስደሰተ ተረድቻለሁ’’ ብለዋል።

“ማንሳት የፈለኩት ሃሳብና ጽሑፎች የሚቀርቡበት እና የሚተረኩበት መንገድ፤ ሕዝብ ከጨቋኝ ስርዓት ስር ለመውጣት የታገለውን፤ በሕዝቦች መካከል የተከሰተ ግጭት አድርጎ ማቅረብ በሕዝቦች የወንድማማችነት ግንኙነት ላይ ተጽእኖ ያሳድራል ለማለት ፈልጌ ነው።’’ በማለት የይቅርታ አድርጉልኝ መልዕክት በገፃቸው አስፍረዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 25 ሚያዚያ 19 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here