በትግራይ ክልል ጊዜአቸው ያለፈባቸው የፀረ አረም ማጥፊያ መድሃኒቶች ለገበሬዎች ሊሰጥ ነው

0
1095

በትግራይ ክልል 1 ሺ 82 ሊትር ጊዜ ያለፈባቸው የፀረ አረም መድሃኒቶች ክምችት ውስጥ 345ቱ የጥቅም ጊዜአቸው ቢያልፍም ለገበሬዎች እንደሚሰጥ የክልሉ የሕብረት ስራ ኤጀንሲ አስታወቀ።
እነዚህ መድሃኒቶች ጊዜአቸው እንዳለፈባቸው ለግብርና ሚኒስቴር ጥቆማ ሰጥጠናል ያሉት የኤጀንሲው የአዝርዕት ግብዓት አቅርቦት ባለሙያ የሆኑት አለባቸው ሓጎስ ነገር ግን ጊዜው ያለፈባቸው መድሃኒቶች ከማስወገድ ይልቅ ለገበሬው እንደሚቀርብ ተናግረዋል።

መድሃኒቶቹ በ2009 የተገዙ ሲሆኑ ገበሬዎቹ ልምድ ማነስ፣ ገበሬዎቹ ዋጋ ተወዶብናል በማለታቸውና ገበሬዎቹ ይጠቀሙት የነበረውን መድሃኒት በአዲሱ (ፓላስ) በቀየሩ የተጠቃሚው ቁጥር በመቀነሱ ክምችቱ እንዲፈጠርና ጊዜው እንዲያልፍ ምክንያት ሆኗል። መድሓኒቱን እንዲጠቀሙት የተለያዩ ሥልጠናዎች ለገበሬዎቹ እየሠጠን በትንሹ ሊጠቀሙት ችለዋል ያሉት አለባቸው ለዚህም 2 ሚልየን 854 ሺ ብር ገንዘብ ወጪ እንደተደረገባቸው ገልፀው አሁን ላይ ያሉት የፀረ አረም መድሃኒቶቹ ጊዜአቸው ቢያልፍም በግብርና ስራ የሚሠሩ እማወራ ገበሬዎች ብቻ እንደሚሰጥ አለባቸው ተናግረዋል።

የተገዙት እነዚህ የፀረ አረም መድሃኒቶች በፈሳሽና በዱቄት መልክ የቀረቡ ቢሆንም ጥቅም ላይ ባለመዋላቸው ገበሬዎች እንደተቸገሩና በየጊዜው ቅሬታቸውን እያሠሙ እንደሆነ በግብርና ሚኒስቴር ስር የሚተዳደረው የፌዴራል ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ ለአዲስ ማለዳ አስታውቋል።

በአምስት ክልሎች የፀረ-አረም ማጥፊያ መድሀኒት ቢገኙም ጊዜአቸው ያለፈባቸው 55 ሺ 282.50 ሊትር፣ 8178 ኪ.ግ በመሆናቸው አገልግሎት ላይ አይውሉም።

ኢትዮጵያ ከፈረመቻቸው በዓለም ጤና ድርጅት ስምምነቶች መሰረት ፀረ አረም በተመረተ በኹለት ዓመት ውስጥ መወገድ ያለበት ቢሆንም ከ1998 አንስቶ ያለፈባቸው ፀረ አረሞች እንዳልተወገደ ለማወቅ ተችሏል። በቅርቡ ካንሰር ሊያስከትሉ የሚችሉ ጊዜ ያለፈባቸው 1600 ቶን ፀረአረም ኬሚካሎች በኦሮሚያና ጋምቤላ ክልሎች መገኘታቸውን አዲስ ማለዳ መዘገቧ ይታወሳል።

ቅጽ 1 ቁጥር 25 ሚያዚያ 19 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here