ከ100 በላይ የቻይና ግዙፍ ኩባንያዎች የተካፈሉበት የቻይና የንግድ ሳምንት ለሦስት ቀናት በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሔደ ያለው ይህ የንግድ ትርኢት ከአፍሪካና መካከለኛው ምሥራቅ ክፍለ አህጉር የተወጣጡ የንግድ ማኅበረሰብ አባላት እየተሳተፉበት ይገኛል። የተመረጡ የቻይና አምራቾች እንዲሁም ከቴክኖሎጂ አቅራቢዎች ጋር የልምድ ልውውጥ የተደረገበት የንግድ ትርኢቱ፥ ካለፈነው ሐሙስ ተጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እንደቀጠለ ይገኛል።
በንግድ ትርኢቱ ላይም ቀላል ኢንዱስትሪዎች እና ጨርቃ ጨርቅ፣ የግንባታ እቃዎች እና ማሽኖች፣ የምግብ እና መጠጥ ማቀነባበሪያ ቴክኖኖጂዎች፣ የቤት ውስጥ መገልገያ እና ፈርኒቸሮች የንግድ ትርኢቱ ትኩረት ከተሰጣቸው መካከል ይገኙበታል። ይህ ለንግድ ባለሙያዎች ብቻ ክፍት የሚሆነው የንግድ ትርኢት ይህንን ዓለም ዐቀፍ የንግድ ትርኢት ከፕራና ኢቨንትስ ጋር በመሆን ያዘጋጀው የኤም.አይ.ኢ ግሩፕ ሊቀ መንበር እና ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆኑት ዴቪድ ዋንግ እንደገለፁት መድረኩ ለአካባቢያዊ የንግድ ማኅበረሰብ አካላት ከግዙፍ የቻይና አምራቾች እና የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ጋር በቀጥታ የግብይት ግንኙነቶችን ለማዳበር ጥሩ አጋጣሚ ይሆናል ብለዋል።
ቅጽ 1 ቁጥር 26 ሚያዚያ 26 ቀን 2011