በእነአብዲ ኢሌ መዝገብ ኹለት ተጨማሪ ሰዎች ተያዙ

0
434

በነአብዲ ኢሌ መዝገብ ተጠርጥረው ክስ የተመሰረተባቸው አባስ ሞሐመድ እና ሻለቃ አብዱላሂ የተባሉ ግለሰቦች ሐሙስ፣ ሚያዚያ 25 ፖሊስ ይዞ ፍርድ ቤት አቀረበ።

በኢትዮ-ሶማሌ ክልል በሐምሌ 2010 በተፈጠረው ኹከትና ብጥብጥ ዐቃቤ ሕግ ክስ ከተመሰረተባቸው 47 ግለሰቦች መካከል አብዲ መሐመድ ዑመር፣ ራህማ መሐመድ ሀይቤ፣ አብዱራዛቅ ሰሀኔ ኢልሚ፣ ፈርሃን ጣሂር በርከሌን ጨምሮ ስድስት ግለሰቦችን ላይ ክስ ማቅረቡ ይታወቃል።

ዐቃቤ ሕግ ለሚዲያ አካላት በሰጠው መግለጨም አብዛኛዎቹ ተጠርጣሪዎች ከክልሉ ጠረፍ ላይ ከመገኘት አኳያ መጥፋታቸውን ገልፆ ከተለያዩ አገራ ጋር ተነጋገሮ ለፍርድ ለማቅረብ እየሠራ መሆኑን ገልፆ ነበር። በቅርብ ጊዜም ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ብርሃኑ ፀጋዬ እንደተናገሩት ተከሳሾቹ ባይያዙም በሌሉበት ክስ መመስረቱ አይቀርም ማለታቸው ይታወሳል።

ቅጽ 1 ቁጥር 26 ሚያዚያ 26 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here