ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የዩኔስኮ የ2019 የሰላም ተሸላሚ ሆኑ

0
433

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና ባሕል ድርጅት /ዩኔስኮ/ የ2019 የሰላም ተሸላሚ ሆኑ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ሽልማት ያገኙት በኢትዮጵያ ሰላምን ለማምጣት፣ ለማስጠበቅና ለማቆየት እንዲሁም የፕሬስ ነፃነት እንዲሰፍን ላደረጉት አስተዋፅኦ መሆኑ ተገልጿል።

በአፍሪካ ኅብረት እየተከበረ ባለው የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን ላይ የዩኔስኮ ዋና ዳይሬክተር አድሪ አዙላይ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የዘንድሮውን የድርጅቱ የሰላም ተሸላሚ መሆንን ይፋ አድርገዋል።

ምርጫውን ያከናወነው ኮሚቴ ውስጥ የላይቤሪያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ እና የፈረንሳይ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ፍራንሷ ኦሎን እንደተካተቱበት ታውቋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 26 ሚያዚያ 26 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here