ትውልደ ኢትዮጵያውያን በባንክ ዘርፍ እንዲሠማሩ ሊፈቀድ ነው

0
579

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሐሙስ፣ ሚያዚያ 24 ባካሄደው ስብሰባ የባንክ ስራ አዋጅን ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ የተወሰኑ ማስተካከያዎችን በማድረግ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲላክ ወሰነ። ካቢኔው ውሳኔው ባንኮች በውጪ አገር እንዲሁም በአገር ውስጥ ያለውን ሀብት በማሰባሰብ ለተለያዩ የልማት ሥራዎች እንዲያውሉ ያግዛልም ብሏል።

መንግሥት ከዚህ ቀደም ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ከፋይናንስ ሴክተሩ እንዲገለሉ በማደረጉ ለከፍተኛ ተቃውሞ እንዲሁም ኪሳራ የዳረገ እንደነበረም ይታወሳል። መንግሥት በአገሪቱ ውሰጥ ያለውን ለውጥ ተከትሎ ትውልደ ኢትዮጲዊያን በአገራቸው ተሳትፎ እንዲያደርጉም ያስችላል ተብሏል።

ምክር ቤቱ የንግድ ምዝገባ ፍቃድ አዋጁን ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ ሕግ ላይም ተወያይቶ በተመሳሳይ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይጸድቅ ዘንድ እንዲተላለፍ ወስኗል። በሠፊው የሚታየውን የንግድ ፈቃድ አገልግሎትን አሰጣጥን ቀልጣፋ፣ ቀላል፣ ወጪ ቆጣቢ እና ዘመናዊ ያደርጋል የተባለው አዋጅ የንግድ ሥራ ቅልጥፍና ላይ ትልቅ አስተዋጽዖ ያደርጋልም ተብሏል።

ቅጽ 1 ቁጥር 26 ሚያዚያ 26 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here