ባሳለፍነው ሳምንት ዓርብ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ በቀረቡት ጥሪ መሰረት ሸገርን ለማስዋብ ፕሮጀክት ግማሽ ቢሊዮን ብር ማበርከቱን አስታወቀ። ባንኩ የከተማዋን ገፅታ በማስዋብና በማሻሻል ነዋሪዎቿን ተጠቃሚ ማድረግ በሚደረጉ አገረዊ ፕሮጀክቶች ላይ ተሳትፎውን እንደሚለውጥም ገልጧል።
ተመሳሳይ ሳምንት ኢትዮ ቴሌኮም አንድ መቶ ሚሊዮን ብር ለፕሮጀክቱ በቅጥር ግቢው ውስጥ ባደረገው ሥነ ስርዓት ላይ የለገሰ ሲሆን በሦስት ዙሮች የተለያዩ ኩባኒያዎች እንዲሁም ግለሰቦች የአምስት ሚሊዮን ብር የእራት ግብዣው ላይ ለመገኘት ቅድሚያ ክፍያቸውን ፈጽመዋል።
የመዝናኛ፣ የማንበቢያ እና የተለያዩ የከተማዋን ገፅታ ይለውጣሉ ተብለው የሚጠበቁ ሥራዎችን እና 56 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው ይህ የወንዞች ዳርቻ ፕሮጀክት የለጋሾች ሥም የሚፃፍበት ሲሆን የቻይና መንግሥትም የፕሮጀክቱን ግንባታ የሚያከናውን ሲሆን ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉም ታወቋል።
ቅጽ 1 ቁጥር 27 ግንቦት 3 ቀን 2011



