ከሕገ ወጥ ንግድ ከ37 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ ማዕድናት በዘጠኝ ወር ተያዙ

0
359

ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ37 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በላይ ማዕድናት በኮንትሮባንድ መንገድ ሲዘዋወሩ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።

በሕገ ወጥ መንገድ ወደ አገር ሊገቡ ሲሉ ከ19 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው እና ሊወጡ ሲሉ ደግሞ ከ18 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ማዕድናት በተለያዩ የጉምሩክ ጣቢያዎች መያዛቸውንም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ያስታወቀ ሲሆን፣ ከነዚህ መካከል 7 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው ወርቅ ነው ተብሏል።

በዚህም ምክንያት ኢትዮጵያ ከወርቅ የምታገኘው የውጪ ምንዛሬ እንደቀነሰ ተነግሯል። ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ ወርቅ ወደ ውጪ በመላክ በዓመት ከ400 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ታገኝ እንደነበር የገለጸው የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፈው ዓመት ያገኘችው 30 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነው ብሏል።

ቅጽ 1 ቁጥር 27 ግንቦት 3 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here