በአገር ዐቀፍ ደረጃ በየዓመቱ 2700 ሰዎች በእብድ ውሻ በሽታ ይሞታሉ

0
538

በኢትዮጵያ ውስጥ በየዓመቱ 2700 ሰዎች በእብድ ውሻ በሽታ እንደሚሞቱ የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሰታወቀ። በተደረገው ጥናት መሰረት ከመቶ ሺሕ ሰዎች ውስጥ 12ቱ በእብድ ውሻ በሽታ የሚያዙ ሲሆን እስከ ኹለት ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸውን ያጣሉ።

ኢንስቲትዩቱ በርካታ ሰዎችን እየገደለ ያለውን የእብድ ውሻ በሽታ ለመከላከልና ለመቆጣጠር ይቻል ዘንድ የተለያዩ ሥራዎችን ከመሥራት ጎን ለጎን ከዚህ ቀደም የነበረውን ላቦራቶሪ በዘመናዊ መሣሪያ እና በሰለጠነ የሰው ኃይል ማጠናከሩን ገልጿል።
በመቀሌና በባሕር ዳር ዘመናዊ ላብራቶሪ በመገንባት ወደ ሥራ ለመግባት ቅድመ ዝግጅቶች ተጠነቋል።

ከጤና ሚኒስቴር፣ ከግብርና ሚኒስቴር የእንሰሳት ጤና የሥራ ሒደት፣ ከዱር እንሰሳት አጠባበቅ ባለሥልጣን፣ ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ፣ እና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተጠሩ ኀላፊዎችና ባለሙያዎች ሚያዝያ 25/2011 የበሽታውን ስርጨት ለመከላከል በተካሔደው የምክክር መድረክ ላይ ተሳትፈዋል::

ቅጽ 1 ቁጥር 27 ግንቦት 3 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here