በቅሸባ ድርጊት የተጠረጠሩ 11 አሽከርካሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

0
402

በጉምሩክ አዋጅ የተደነገገውን የአጓጓዥ ግዴታዎች ባለመወጣት (በቅሸባ ድርጊት ተሳትፈዋል ተብለው) የተጠረጠሩ ከጅቡቲ አዲስ አበባ ብረት በማጓጓዝ የተሰማሩ 11 አሽከርካሪዎች ሚያዝያ 29/2011 በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ሰራተኞች አማካኝነት በቁጥጥር ስር ዋሉ። ተጠርጣሪዎቹ በድምሩ 3700 ኪሎ ግራም ብረት እንደቀሸቡ ተገልጿል።

በአንድ ድርጅት ሥም ከጅቡቲ አዲስ አበባ እንዲገባ ፍቃድ የተሰጠውን የላሜራ ብረት በማጓጓዝ ላይ የነበሩ አሽከርካሪዎች ብረቱን በመንገድ ላይ በመቀነስ የሚዛን ልዩነት እንዳያመጣባቸው በተቀሸበው ብረት ምትክ በተሽከርካሪው ላይ ባሉ ክፍት ቦታዎች ቁሳ ቁሶችን ጨምረዋል።

በተሸከርካሪዎቹ ኪሶች፣ የነዳጅ ታንከሮች ፣ የመኪናው ፊተኛ ክፍል ውስጥ ድንጋይ፣ ከ200 ሌትር በላይ ውሃ እንዲሁም እስከ 20 ኩንታል የሚሆን ከሰል በመጫንና በመመዘን የቅሸባ ድርጊት ፈፅመዋል በሚል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ያሳወቀው የገቢዎች ሚኒስቴር ለተጨማሪ ምርመራ ለፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ እንዲተላለፉ መደረጋቸውም ተናግሯል።

ቅጽ 1 ቁጥር 27 ግንቦት 3 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here