የምግብና መጠጥ ማቀነባበር ቴክኖሎጂ ላይ ያተኮረ ዓውደ ርዕይ እየተካሔደ ነው

0
272

ሦስተኛው የኢትዮጵያ የግብርና፣ ምግብና መጠጥ ቴክኖሎጂ እንዲሁም ፕላስቲክ ማሸጊያ የንግድ ትርዒት ለሦስተኛ ጊዜ በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሔደ ነው። ኢትዮጵያ ገበያ ፍለጎት የተዘጋጁ መፍትሔዎች እና ቴክኖሎጂዎች የቀረቡበት ኤግዚቢሽን ከ18 በላይ አገራት፣ ከ148 በላይ ዓለም ዐቀፍ የንግድ እና የቴክኖሎጂ ድርጅቶች የተሳተፉበት ሲሆን ግንቦት 1 የጀመረው ትርኢቱ ዛሬ ይጠናቀቃል።

በጀርመኑ የንግድ ትርኢት አዘጋጅ ፌር ትሬድ እና በኢትዮጵያው ፕራና ኢቨንትስ የተዘጋጀው ኤግዚቢሽን ለመጀመሪያ ጊዜ የጀርመን፣ የኔዘርላንድ እና የቱርክ ብሔራዊ ተሳትፎ የታየበት ነበር።

የግብርና ዘርፉን ለማዘመን በኢትዮጵያ የሚደረጉ የተያዩ ጥረቶችን ያዘምናል የተባለው ኤግዚብሽኑ የንግዱ ማኅበረሰብ በነፃ ገብቶ ምረቶቹን የጎበኘ ሲሆን በቀጣይም በአጋርነት ለመሥራት የተለያዩ አጋርነቶች የተፈጠሩበት እንደነበረም ተገልጿል።

ቅጽ 1 ቁጥር 27 ግንቦት 3 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here