ሦስት አዳዲስ የካንሰር ሕክምና መስጫ መሣሪያዎች ተገጠሙ

0
767

በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ብቻ ሲሰጥ የነበረውን ካንሰርን በጨረር የማከም ሕክምና ለማሻሻል አንድ ተጨማሪ ማሽን ገጠማ መጠናቀቁን እና በጅማ ሆስፒታልም አንድ የጨረር ማሽን መገጠሙን የጤና ሚኒስቴሩ አሚር አደም ገለፁ፡፡ አንድ ተጨማሪ የጨረር ሕክምና መስጫ ማሽን በሐሮማያ በመገጠም ላይ ሲሆን የገጠማ ሥራው 80 በመቶ መድረሱንም ጠቁመዋል፡፡

በኢትዮጵያ የካንሰር ሕሙማን ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ጥናቶች ያመላክታሉ። መንግሥት በመቀሌ፣ በሐዋሳ፣ በሐሮማያ፣ በጅማ እና ጎንደር ከተሞች የካንሰር ሕክምና ሆስፒታሎችን በማስገንባት ላይ ሲሆን የጅማ እና የሐሮማያ ሆሰፒታሎች አዳዲሶቹን የጨረር ሕክምና መሣሪያዎች ከገኙት መካከል ናቸው፡፡

በአሁኑ ወቅት 13 የካንሰር ሐኪሞች ብቻ በኢትዮጵያ ውስጥ ሲኖሩ በየዓመቱ 160 ሺሕ አዳዲስ የካንሰር ታካሚዎች ወደ ሕክምና ጣቢያዎች ይመጣሉ፡፡ የጡት ካንሰር 33 በመቶ ለሚሆነው የካንሰር ሞት ምክንያት ሲሆን የማሕጸን ጫፍ ካንሰር 26 በመቶ የሚሆነውን የካንሰር ሞት ያስከትላል፡፡

ቅጽ 1 ቁጥር 28 ግንቦት 10 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here