የሕፃናት እና የነፍጡሮች የምግብ እጥረት

0
524

በአማራ፣ በደቡብ፣ ሶማሌና ኦሮሚያ ክልሎች ከምግብ እጥረት ጋር በተያያዘ ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ 315 ሺሕ 594 ሕፃናቶች የምግብ እጥረት ማጋጠሙ የተለየ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 14625ቱ የምግብ ሕክምና እንዲያገኙ መደረጉ ተገልጿል። በተጨማሪም 131 ሺሕ 680 ነብሰ ጡርና የሚያጠቡ እናቶች የምግብ እጥረት እንዳጋጠማቸው ተለይቶ ለ13 ሺሕ 820 የምግብ ሕክምና ተሰጥቷቸዋል።

በተመሳሳይም የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለተፈናቃይና ተመላሽ ወገኖች የጤና ክትትል በማድረግ ላይ ይገኛል። ከዚህም ጋር በተያያዘ ባለፉት ሦስት ሳምንታት ውስጥ በአማራ፣ ትግራይ፣ ሶማሌ፣ ሐረሪ፣ ኦሮሚያና ደቡብ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ 76 ወረዳዎች በአጠቃላይ ከ38 ሺሕ በላይ ሰዎች የሕክምና አገልግሎት ያገኙ ሲሆን በታካሚዎች በብዛት የታዩት በሽታዎች የመተንፈሻ አካላት ችግር፣ የአይን ሕመም፣ እከክ፣ ተቅማጥ፣ የሆድ ትላትልና የሳንባ ምች ናቸው።

ባለፈው ሳምንት አዲስ ማለዳ በአምስት ክልሎች በሚገኙ 65 ወረዳዎች ውስጥ ባሉ መጠለያ ጣቢያዎች እስከ ሚያዝያ 2011 ድረስ 16 ሺሕ 361 ነፍሰ ጡሮች ክትትል እያደረጉ እንደሚገኙ እና 734 የሚሆኑ እናቶችም መውለዳቸውን የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ማስታወቁን መዘገቧ ይታወሳል።

ቅጽ 1 ቁጥር 28 ግንቦት 10 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here