የኬኒያው ኢኩዊቲ ባንክ በአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ለመክፈት እየተዘጋጀ ነው

0
297

በምሥራቅ አፍሪካ መሪ ከሆኑት ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው የኬኒያ የኢኩዊቲ ባንክ በዓመቱ መጨረሻ በአዲስ አበባ ቅርንጫፍ በመክፈት በአፍሪካ ኹለተኛ ግዙፍ የሆነውን የኢትዮጵያ ገበያ ለመቀላቀል ማሰቡን አስታወቀ። ባንኩ በዚህ ዓመት ወደ ተለያዩ የአፍሪካ አገራት ለመግባት ባሰበው መሰረት ኢትዮጵያን ግንባር ቀደም ተመረጭ ማድረጉን አክሎ ለረጅም ዓመታት ለፋይናንስ ሴክተር ኢንቨስትመንት ዝግ የነበረው የኢትዮጵያ ገበያ አሁን የተሸለ በመሆኑ ይህንን ዕድል ለመጠቀም መወሰኑንም ተናግሯል።

በአፍሪካ ካሉ ትልልቅ ባንኮች አንዱ ከሆነው የኬኒያ ኢኩዊቲ ባንክ ባሻገር በቅርቡ መዋሐዳቸውን ይፋ ያደረጉት የኬኒያ ንግድ ባንክ እና የኬኒያ ብሔራዊ ባንክም ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ለመቀላቀል ማሰባቸውን ማሳወቃቸው ይታወቃል።

ቅጽ 1 ቁጥር 28 ግንቦት 10 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here