በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን 31 ሚሊዮን ብር ለተፈናቃዮች ሰበሰቡ

0
500

በዓለም ዐቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት በኩል ላለፉት ወራት የተሰበሰበው እና ለጌዲዮ ተፈናቃዮች በተለያዩ የገንዘብ መሰብሰቢያ አማራጮች ሲሰበሰብ የቆየውን 31 ሚሊዮን 400 ሺሕ ብር ወደ ተግባር ለመስገባት ሥራ ጀመረ፡፡ በትብበሩ ፕሬዘዳንት ታማኝ በየነ እና በወርልድ ቪዥን መካከል ግንቦት 7/2011 በተደረገ ስምምነት ገንዘቡ 70 ሺሕ ሰባ ኹለት ለሚሆኑ ተፈናቃይ ወገኖች በሚተገበረው ፕሮጀክት አማካኝነት እንደሚደርስም ተነግሯል።ወርልድ ቪዥን በበኩሉ ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ በማድረግ ለፕሮጀክቱ የሚውለውን የሥራ ማስኬጃ እንደሚደግፍ እና ጎን ለጎንም የግጭቱን መንስኤ ለመመርመር እና አስተማማኝ ሰላም በአካባቢው እንዲሰፍን ለማድረግ ለሚሠሩ ሥራዎች መነሻ የሚሆን ነው ብለዋል፡፡

ታማኝ በሥነ ስርዓቱ ወቅት እርዳታው በሰብኣዊነት እና በኢትዮጵያዊነት የተደረገ እንጂ ከምንም ዓይነት ብሔር ወይም አካባቢ ጋር የማይገናይ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

ለአንድ ዓመት በሚቆየው በዚህ ፕሮጀክት አንድ ወር ውስጥ ቅድመ ዝግጅቶቹን አጠናቆ ወደ ሥራ የሚገባ ሲሆን መንግሥትም የራሱ ሚና እንደሚኖረው ተነግሯል።

ቅጽ 1 ቁጥር 28 ግንቦት 10 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here