“ጠቅላይ ሚኒስተሩ ይቅርታ ባይጠይቁም ይቅር ብለናቸዋል” የሕክምና ማኅበር

0
579

የኢትዮጵያ ሕክምና ማኅበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሕክምና ባለሙያዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ልባችን ተሰብሯል ሲል ሐሙስ፣ ግንቦት 8 በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቀ፡፡ የማኅበሩ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ገመቺስ ማሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የምንወዳቸው፣ የምናከብራቸውና ለሁላችንም አርዓያ የሚሆኑ መሪ ቢሆኑም በአገራችን ስመጥሩ የሕክምና ባለሙያዎች ባልጠፉበት ሁኔታ አንድም ባለሙያ አለማመስገናቸው መላውን የሕክምና ባለሙያዎች እንዳሳዘ ገልጸዋል፡፡

የሕክምና ሙያ የሚጠይቀውን ግዴታዎች እየተወጣ መብቱን ለማስከበር እንደሚሰራ ማኅበሩ በሰጠው መግለጫ ላይ አመልክቶ መንግሥትም ዘርፉ ላይ እየታዩ ያሉ ክፍተቶችን ለማሻሻል ለዘርፉ ትኩረት እንዲሰጥ አሳስቧል። ማኅበሩ በመግለጫው 12 አቋሞቹን የዘረዘረ ሲሆን በተለይ መንግሥት የአገሪቱን ጤና ፖሊሲ ወቅቱ የሚጠይቀውን ሪፎርም መሰረት በማድረግ የጤናውን ዘርፍ የሰው ኀይል ትኩረት ባደረገ መልኩ ሊከለስና ተግባራዊ ሊደረግ እንደሚገባ አሳስቧል፡፡ በተጨማሪም ኢትዮጵያ ለጤናው ዘርፍ የምትመድበውን በጀት በተመሳሳይ የዕድገት ደረጃ ላይ የሚገኙ አገራት ጋር ሲነፃፀር ዝቅተኛ በመሆኑ ማሻሻያ ሊደረግበት ይገባል ሲል ማኅበሩ እምነቱን ገልጿል፡፡

ሚያዚያ 26 በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በተደረገው የውይይት መድረክ ላይ ከመላው አገሪቱ የተወጣጡ ከ3 ሺሕ በላይ የሕክምና ባለሙያዎች መገኘታቸው ይታወሳል፡፡

ቅጽ 1 ቁጥር 28 ግንቦት 10 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here