የጌታቸው አሰፋ ጉዳይ

0
600

ባለፈው ሳምንት የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለቀድሞ የብሔራዊ ደኅንነትና መረጃ ዋና ኃለፊ ጌታቸው አሰፋ የፍርድ ቤት መጥሪያ ካወጣባቸው ዕለት ጀምሮ ጉዳዩ በማኅበራዊ ትስስር አውታሮች ከፍተኛ የመነጋገሪያ ብቻ ሳይሆን የመነታረኪያ ርዕሰ ጉዳይ ሆኗል።

በአንድ በኩል ማንኛውም ተጠርታሪ ፍርድ ቤት የመቅረብና ፍትሕ የማግኘት መሰረታዊ መብት አለው በማለት የጌታቸው አሰፋ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ግድ ነው የሚል ሙግት ያቀርባሉ። ማንኛውም ሰው በሕግ ፊት እኩል ከሆነ የጌታቸው ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ትዕዛዝ መውጣቱ አያስገርምም። ቀርበው ንፁሕነታውን ማስረዳት አለባቸው። አለፍም ሲል አንዳንዶች ጌታቸውን ከፍርድ በፊት የብዙዎችን ሕይወት ቀጥፈዋል፣ ኢሰብኣዊ ድርጊት ፈጽመዋል በሚሉ ለስላሰ ሐረጋት ሲወነጅሉ ሌሎች ደግሞ ጠንከር ባሉ ሐረጋት ‘ነፍሰ በላው’፣ ‘ነፍሰ ገዳዩ’ በሚል ፎቷቸውን በመጠቀም ዘመቻቸውን ቀጥለዋል።

በሌላ ጽንፍ ደግሞ የጌታቸው የፍርድ ቤት መጥሪያ ፖለቲካዊ አንድምታ ያለው ነው ብለው የሚሞግቱም አሉ። ቀላል የማይባሉት በትግራይ ብሔራዊ ክልል የሚገኙ ሰዎች የጌታቸው ወደ ፍርድ ቤት መጠራት ሆን ተብሎ የትግራይ ሕዝብን ለማጥቃት የተጎነጎነ ሴራ ነው ሲሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በማሰማት ላይ ናቸው። በአንዳንድ ወጣቶች አነሳሽነት በትግራይ ውስጥ “እኔም ጌታቸው ነኝ” የሚል ቲሸርት በማሰራት በሰፊ በማሰራጨት ላይ መሆናቸው በማኅበራዊ ገፆች የሚለቁት ፎቶዎች ምስክር ናቸው። ከዚህም ባለፈ አስተባባሪ ናቸው የተባሉ ሦስት ወጣቶች ቲሸርቱን በማድረግ ለጌታቸው አሰፋ አጋርነታቸውን ለመግለጽ ሰልፍ መጥራታቸው ታውቋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 28 ግንቦት 10 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here