10ቱ ብዙ ማንበብ እና መፃፍ የሚችሉ ሴቶች ቁጥር ያላቸው አገራት

0
717

ምንጭ፡-የዓለም ባንክ

በኢትዮጵያ የመሰረታዊ ትምህርት መስፋፋት በወታደራዊው መንግሥት ደርግ “መሰረተ ትምርህርት” ዘመቻ በሰፊው ተጀምሮ የነበረ ሲሆን ይህም በተለይ በገጠሩ ክፍል ለሚኖሩ ጎልማሶች መልካም አጋጣሚ መፍጠሩን መዛግብት ያስረዳሉ’ ከደርግ ውድቀት በኋላም ረጀም ዓመታትን የፈጀው የትምህር ዘርፉን የመለወጥ ሥራ እ.ኤ.አ 2000 ድረስ እንብዛም ለውጥ ሳያሳይ ቆይቷል።

በርሊን ኢንስቲትዩት በያዝነው ዓመት በሠራው የዳሰሳ ጥናት እንደሚያሳይው በ2000 በኢትዮጵያ ከሦስት ሴቶች አንዷ ብቻ ወደ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመግባት ዕድል ታገኝ ነበር’ በተመሳሳይ ጥናት እንደተመለከተው ከ9 ዓመት እስከ 12 ዓመት ከሆናቸው 10 ሴቶች መካከል ሰባቱ ትምህርት ቤት ደጅ ደርሰው የማያውቁ የነበሩ ሲሆን እ.ኤ.አ 2016 በተሠራው ጥናት ደግሞ ቁጥሩ ወደ ኹለት ዝቅ ብሎ ነበር።

እንደ ወርልድ ባንክ መረጃ በኢትዮጵያ መሰረታዊ የሆነው የመፃፍ እና ማንበብ ችሎታ ያላቸው ሴቶች ቁጥር ግን አሁንም ዝቅተኛ ነው።

ቅጽ 1 ቁጥር 28 ግንቦት 10 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here