የአምስት ፓርቲዎች ውሕድ የሆነው የኅብር ፓርቲ ምሥረታ ተካሔደ

0
361

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሽግግር ምክር ቤት፣ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ንቅናቄ፣ ቱሳ የኢትዮጵያ ትንሳኤ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት፣ የኦሞ ሕዝቦች ዲምክራሲያዊ ኅብረት እና ደቡብ ኢትዮጵያ አረንጓዴ ኮከቦች ቅንጅት ናቸው

በአገር ውስጥና በውጭ አገር ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አምስት ፓርቲዎች አገራዊ ፓርቲ ሆነው ውሕደት ፈጽመዋል፡፡ “ኅብር ፓርቲ” የሚል መጠሪያ ያገኘው ድርጅቱ ባሳለፍነው ሐሙስ፣ ግንቦት 8 የምሥረታ ጉባኤውን አካሒዷል፡፡
በዕለቱ ውሕደት የፈጸሙት ፓርቲዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሽግግር ምክር ቤት፣ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ንቅናቄ፣ ቱሳ የኢትዮጵያ ትንሳኤ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት፣ የኦሞ ሕዝቦች ዲምክራሲያዊ ኅብረት እና ደቡብ ኢትዮጵያ አረንጓዴ ኮከቦች ቅንጅት ናቸው፡፡

ተመሳሳይ ሐሳብ የሚያራምዱ ፓርቲዎች መጣመራቸው ለአገሪቱ ፖለቲካ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸው እና ለሕዝቡም የተሻለ አማራጭ ይዘው እንደሚቀርቡ በጉባኤው ላይ ንግግር ያደረጉ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ፓርቲው የመተዳደሪያ ደንብ እና የፖለቲካ ፕሮግራማቸውን በይፋ ለተከታዮቻቸው ማሳወቃቸውን ለአዲስ ማለዳ የገለጹት የአዲሱ ፓርቲ ሊቀመንበር ግርማ በቀለ የኅብር ፓርቲ የሚከተለው ለዘብተኛ ሊብራል ርዕዮተ ዓለም እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በአገሪቱ ውስጥ ለረዥም ጊዜ የቆየውን ማኅበራዊ ምስቅልቅል፣ ያልተመለሱ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎች ምላሽ ባለማግኘታቸው ለእነዚህ ምላሽ ለመስጠት በኅብረት መቆም ግድ ብሎናል ያሉት ሊቀመንበሩ፣ አዲሱ ፓርቲ ለእነዚህ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የአጭር፣ የመካከለኛና የረዥም ጊዜ ዕቅድ ይዞ በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡

ቅጽ 1 ቁጥር 28 ግንቦት 10 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here