የኢትዮጵያ የስንዴ ግዢ ካለፈው ዓመት 18 በመቶ ቀነሰ

0
627

ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር የስንዴ ግዢ መፈፀሙን አገልግሎቱ ለአዲስ ማለዳ የላከው ሪፖርት ያሳያል።

የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የ2011 በጀት ዓመት በዘጠኝ ወራት የ755 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ስንዴ ግዥ የፈፀመ ሲሆን፥ ተጠናቀው መፈረም የነበረባቸው ሰባት የማዕቀፍ ሥምምነት ግዥዎችን ማጠናቀቅ ባለመቻሉ እንዲሁም ባለፈው የበጀት ዓመት ከፍተኛ የስንዴ ምርት በመገዛቱ ምክንያት ቅናሽ ማሳየቱን አስታወቀ።

ለግብርና እና እንስሳት ሀብት ሚኒስቴር የ155 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ስንዴ ግዥ በ1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር እና ለኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የ600 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ስንዴ በ4 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ባጠቃላይም የ5 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር የስንዴ ግዢ መፈፀሙን አገልግሎቱ ለአዲስ ማለዳ የላከው ሪፖርት ያሳያል።

የፌዴራል ባለበጀት መሥሪያ ቤቶችና የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የማዕቀፍ ሥምምነት ግዥ ውስጥ በሎት 1 (ምድብ አንድ) የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዕቃዎች ግዥና የ755 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ስንዴ ግዥ በመፈፀም በጠቅላላው ብር 8 ቢሊዮን 481 ሚሊዮን 461 ሺሕ 72 ብር በሚሆን ዋጋ የአሸናፊነት ደብዳቤ ለተጫራቾች መሰጠቱን አዲስ ማለዳ ከመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ያገኘችው መረጃ ያመለክታል።

በተጨማሪም አገልግሎቱ በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ከተለያዩ የአገር ውስጥ እና የውጭ አገር አቅራቢዎች የቃሊቲ መናኸሪያ ግንባታ ግዥ፣ የትራንስፖርትና ትራፊክ ማኔጅመንት ማሠልጠኛ ኢንስቲትዩት ግንባታ ግዥ መፈፀሙንም ተናግሯል።
ለፌዴራል ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች ከ2011 አስከ 2013 በጀት ዓመት የማዕቀፍ ሥምምነት ግዥ የሎት 1 (ምድብ አንድ) የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዕቃዎች ግዥ በብር 668 ሚሊዮን፣ ለመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ከ2011 እስከ 2013 በጀት ዓመት የማዕቀፍ ሥምምነት ግዥ የሎት 1 የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዕቃዎች ግዥ በብር 1.4 ቢሊዮን ብር የአሸናፊነት ደብዳቤ እንደተሰጣቸው ለማወቅ ተችሏል።

ለትራንስፖርት ባለሥልጣን የቃሊቲ መናኸሪያ ግንባታ ግዥ 445 ቢሊዮን ብር፣ የትራንስፖርትና ትራፊክ ማኔጅመነት ማሠልጠኛ ኢንስቲትዩት ግንባታ ግዥ 381 ሚሊዮን ብር፣ ለግብርና እና እንስሳት ሀብት ሚኒስቴር የ155 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ስንዴ ግዥ በድምሩ በ1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር የአሸናፊነት ደብዳቤ መሰጠቱንም ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በአጠቃላይ በ2011 በጀት ዓመት በዘጠኝ ወራት ውስጥ በ8 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር የአሸናፊነት ደብዳቤ ለአሸናፊ ድርጅቶች የተሰጠ ሲሆን፣ ተጠቃሚ መሥሪያ ቤቶች ቴክኒካል ገምጋሚዎችን በወቅቱ ያለመላክና ለሚፈፀምላቸው ግዥ ያላቸውን በጀት በአፋጣኝ አለማሳወቅ፣ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ የገበያ ዋጋ መረጃ ጥናት መዘግየት፣ የኢትዮጵያ የተሥማሚነት ምዘና ድርጅት ቤተ ሙከራ ውጤት መዘግየት እና በመጣውም ውጤት ላይ በአቅራቢዎች በርካታ ቅሬታ መፈጠሩ ዋና ዋና ችግሮች ሆነው ተለይተዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 29 ግንቦት 17 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here